ዘዳግም 5:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፥ ዛሬ የምነግራችሁን ሕግና ሥርዓት ሁሉ አድምጡ፤ በጥንቃቄም አጥንታችሁ እነዚህን ትእዛዞች ጠብቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እስራኤል ሆይ፤ በዛሬዋ ዕለት በጆሯችሁ የምነግራችሁን ሥርዐትና ሕግ ስሙ፤ አጥኗቸው፤ በጥንቃቄም ጠብቋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እስራኤል ሆይ፥ እንድትማሩአት በማድረግም እንድትጠብቁአት ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራትን ሕግና ሥርዓት ስሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ አላቸው፥ “እስራኤል ሆይ እንድትማሩአትም፥ በማድረግም እንድትጠብቁአት ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራትን ሥርዐትና ፍርድ ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ አላቸው፦ እስራኤል ሆይ፥ እንድትማሩአት በማድረግም እንድትጠብቁአት ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራትን ሥርዓትና ፍርድ ስሙ። |
እንዲህም አላቸው፤ “በጥሞና ትእዛዞቼን ብታዳምጡና በፊቴ መልካም የሆነውን ነገር በታዛዥነት ብታደርጉ፥ ኅጎቼንም ሁሉ ብትጠበቁ፥ በግብጻውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች በአንዱ እንኳ አልቀጣችሁም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
ከዮርዳኖስ ማዶ አራባ በሚባል ምድረ በዳ በሱፍ ፊት ለፊት በአንድ በኩል ፋራን፥ በሌላ በኩል ጦፌል፥ ላባን፥ ሐጼሮትና ዲዛሃብ መካከል ሳሉ ሙሴ ለእስራኤል ሕዝብ ያደረገው ንግግር ይህ ነው።
“የቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ምድር በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ በጥንቃቄ የምትጠብቁአቸው ኅጎችና ሥርዓቶች እነዚህ ናቸው፤
ይህን መጽሐፍ አጠገቡ በማኖር በዘመኑ ሁሉ ያንብበው፤ ይህንንም ቢያደርግ እግዚአብሔርን ማክበርና በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉትንም ሕጎችና ደንቦች በጥንቃቄና በታማኝነት መፈጸምን ይማራል።
“ነገር ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ባትታዘዝና እኔ ዛሬ የምሰጥህንም ሕጎችና ትእዛዞች በታማኝነት ባትጠብቅ ከዚህ የሚከተለው መርገም ሁሉ ይደርስብሃል፦
“እነሆ፥ ዛሬ እናንተ የየነገድ መሪዎቻችሁ፥ ሽማግሌዎቻችሁ፥ ሹሞቻችሁ፥ ሌሎችም የእስራኤል ወንዶች ሁሉና ልጆቻችሁ፥ ሴቶቻችሁ፥ በእናንተ ሰፈር ሆነው እንጨት የሚለቅሙላችሁና ውሃ የሚቀዱላችሁ መጻተኞች፥ ሁላችሁም በእግዚአብሔር አምላካችሁ ፊት ቆማችኋል።
ከዚህ በኋላ ሙሴ ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “እስራኤል ሆይ፥ አሁን እንግዲህ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ ለመውረስ ያበቃችሁ ዘንድ የማስተምራችሁን ሕግና ሥርዓት አዳምጣችሁ በሥራ ላይ አውሉት።
ይህም ምድር ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ ያለውን ግዛት ሁሉ በማጠቃለል በስተደቡብ እስከ ጨው ባሕር፥ እንዲሁም በስተምሥራቅ እስከ ፒስጋ ተራራ ግርጌ የሚደርስ ነው።
“እግዚአብሔር አምላኬ እንድነግራችሁ ያዘዘኝን ሕግና ሥርዓት ሁሉ አስተምሬአችኋለሁ፤ እርስዋን ለመውረስ በምትገቡባት ምድር ስትኖሩ እነዚህን ትእዛዞች አክብሩ።
ይህን የሕግ መጽሐፍ ምን ጊዜም ከማንበብ አትቈጠብ፤ በእርሱ የተጻፈውን ሁሉ መፈጸም ትችል ዘንድ እርሱን ሌሊትና ቀን አሰላስለው፤ ይህንን ብታደርግ፥ ሁሉ ነገር በተቃና ሁኔታ ይሳካልሃል።