ዘዳግም 30:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ዛሬ እኔ ሕይወትንና መልካምነትን ወይም ሞትንና ክፋትን እንድትመርጥ ሰጥቼሃለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ ዛሬ ሕይወትንና በረከትን፣ ሞትንና ጥፋትን በፊትህ አኑሬአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ፤ ዛሬ ሕይወትንና መልካምነትን፥ ሞትንና ክፋትን በፊትህ አኑሬአለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እነሆ፥ ዛሬ በፊትህ ሕይወትንና ሞትን፥ መልካምነትንና ክፉነትን አኑሬአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተመልከት፤ ዛሬ በፊትህ ሕይወትንና መልካምነትን፥ ሞትንና ክፋትን አኑሬአለሁ። |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ብዬ እንድናገር አዘዘኝ፦ “እነሆ አድምጡ! እኔ እግዚአብሔር ወደ ሕይወት የሚወስደውንና ወደ ሞት የሚያደርሰውን መንገድ በፊታችሁ አኑሬአለሁ፤ ከሁለቱ አንዱን ምረጡ፤
እነሆ ዛሬ እኔም መልሱን ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድነግራችሁ በእኔ አማካይነት ለላከላችሁ ቃል ሁሉ ታዛዦች አልሆናችሁም።
እግዚአብሔር መልካም የሆነውንና ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል፤ ይኸውም ፍትሕን እንድትጠብቅ፥ ደግነትን እንድትወድ፥ ከአምላክህ ጋር በትሕትና እንድትመላለስ ነው።
እነሆ፥ እኔ በሕይወትና በሞት መካከል፥ በእግዚአብሔር በረከትና መርገም መካከል ምርጫ እሰጣችኋለሁ፤ በምታደርጉትም ምርጫ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ ምስክር አድርጌ እጠራለሁ፤ ስለዚህም እናንተና ዘሮቻችሁ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጡ።
ይህ ሕግ የባዶ ቃላት ቅንብር አይደለም፤ እርሱ የሕይወታችሁ መሠረት ነው፤ ስለዚህ ለዚህ ቃል ታዛዦች ሁኑ፤ ይህን ብታደርጉ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሱአት ምድር ለረዥም ዘመን ትኖራላችሁ።”