La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 28:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በምትሞትበትም ጊዜ ወፎችና የምድረ በዳ አራዊት ሥጋህን ይበሉታል፤ የሚያባርራቸውም አይኖርም፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሬሳህ የሰማይ አሞሮችና የምድር አራዊት ሲሳይ ይሆናል፤ በማስፈራራትም የሚያባርራቸው አይኖርም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሬሳህ የሰማይ አሞሮችና የምድር አራዊት መብል ይሆናል፤ የሚያባርራቸውም አይኖርም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሬሳህ ለሰ​ማይ ወፎች ሁሉ፥ ለም​ድ​ርም አራ​ዊት መብል ይሆ​ናል፤ የሚ​ቀ​ብ​ር​ህም አታ​ገ​ኝም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሬሳህ ለሰማይ ወፎች ሁሉ ለምድርም አራዊት መብል ይሆናል፥ የሚያስፈራቸውም የለም።

Ver Capítulo



ዘዳግም 28:26
11 Referencias Cruzadas  

በአባቱ የሚያፌዝና እናቱ በምታረጅበት ጊዜ የሚንቃት ሰው የሸለቆ ቊራዎች ዐይኖቹን ጐጥጒጠው ያወጡታል፤ ጆፌ አሞራዎችም ይበሉታል።


ሬሳቸው የትም ተጥሎ ይበሰብሳል እንጂ አይቀበርም፤ ተራራዎችም በደማቸው ይጥለቀለቃሉ።


እኔ እግዚአብሔር አራት ክፉ ነገሮች እንዲደርሱባቸው ወስኛለሁ፤ ስለዚህ በጦርነት ይሞታሉ፤ ሬሳቸውን ውሾች ይጐትቱታል፤ ወፎች ሥጋቸውን ይበሉታል፤ የተረፈውን አራዊት ይግጡታል፤


ሁሉም በአሠቃቂ በሽታ ያልቃሉ፤ የሚያለቅስላቸውም ሆነ የሚቀብራቸው እንኳ አያገኙም፤ ሬሳቸው እንደ ጒድፍ በሜዳ ላይ ይከመራል፤ በጦርነትና በራብ ያልቃሉ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ምግብ ይሆናል።


የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ያቀዱት ነገር ሁሉ በዚህ ስፍራ እንዳይፈጸም አደርጋለሁ፤ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና በጦርነትም እንዲገድሉአቸው አደርጋለሁ፤ ሬሳቸውንም የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት እንዲበሉት አደርጋለሁ።


ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚፈልጉ ጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ሬሳቸውንም ሁሉ የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ይበሉታል።


ሬሳቸውም የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ሲሳይ ይሆናል፤ አስፈራርቶ የሚያባርርላቸውም አይኖርም።


“በዚያን ጊዜ የይሁዳ ነገሥታትና የመኳንንት ዐፅሞች እንዲሁም የካህናቱና የነቢያቱ የሌላውም የኢየሩሳሌም ነዋሪ ሕዝብ ዐፅሞች ሁሉ ከየመቃብሩ ተለቅመው ይወጣሉ።