የቀዓት የበኲር ልጅ ዓምራም፥ የአሮንና የሙሴ አባት ነበር፤ አሮንና ዘሮቹ ለዘለቄታው ለንዋያተ ቅድሳት ኀላፊዎች እንዲሆኑ፥ እግዚአብሔርን በማምለክ ሥነ ሥርዓት ላይ ዕጣን እንዲያጥኑ፥ እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉና በስሙም ሕዝቡን እንዲባርኩ ተለይተው ነበር፤
ዘዳግም 21:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱን እንዲያገለግሉት፥ በእርሱ ስም እንዲባርኩ፥ የክርክርና የወንጀል ጉዳይ በእነርሱ እንዲወሰን አምላክህ እግዚአብሔር ካህናቱን የሌዊን ልጆች ስለ መረጣቸው ወደ አስከሬኑ ይቅረቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲያገለግሉና በእግዚአብሔር ስም እንዲባርኩ፣ በማንኛውም የክርክርና የጥቃት ጕዳዮች ሁሉ ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ፣ አምላክህ እግዚአብሔር መርጧቸዋልና የሌዊ ልጆች ካህናቱ ወደ ፊት ይቅረቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲያገለግሉና በጌታ ስም እንዲባርኩ፥ በማንኛውም የክርክርና የጥቃት ጉዳዮች ሁሉ ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ፥ አምላክህ ጌታ መርጦአቸዋልና የሌዊ ልጆች ካህናቱ ወደ ፊት ይቅረቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሌዊ ልጆች ካህናትም ይቀርባሉ፤ በፊቱ እንዲያገለግሉ፥ በስሙም እንዲባርኩ አምላክህ እግዚአብሔር መርጦአቸዋልና፤ በእነርሱም ቃል ክርክር ሁሉ ጕዳትም ሁሉ ይቆማልና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሌዊ ልጆች ካህናትም ይቀርባሉ፤ በፊቱ እንዲያገልግሉ፥ በስሙም እንዲባርኩ አምላክህ እግዚአብሔር መርጦአቸዋልና፥ በእነርሱም ቃል ክርክር ሁሉ ጉዳትም ሁሉ ይቈረጣልና፤ |
የቀዓት የበኲር ልጅ ዓምራም፥ የአሮንና የሙሴ አባት ነበር፤ አሮንና ዘሮቹ ለዘለቄታው ለንዋያተ ቅድሳት ኀላፊዎች እንዲሆኑ፥ እግዚአብሔርን በማምለክ ሥነ ሥርዓት ላይ ዕጣን እንዲያጥኑ፥ እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉና በስሙም ሕዝቡን እንዲባርኩ ተለይተው ነበር፤
በከተሞች ከተቀመጡት ከወገኖቻችሁ ወደ እናንተ የሚመጣ ጉዳይ፥ የግድያ፥ ወይም ሌላ የሕግ ጉዳይ፥ ሕግን፥ ትእዛዞችን ወይም ድንጋጌና ሥርዓቶችን መተላለፍ ቢሆን በእግዚአብሔር ላይ በደል እንዳይፈጽሙ፥ ቊጣም በእናንተና በወንድሞቻችሁ ላይ እንዳይመጣ አስጠንቅቁአቸው፤ እንዲህም ብታደርጉ በደለኞች አትሆኑም።
ያም ሰው እንዲህ አለኝ፦ “ከቤተ መቅደሱ ባዶ ቦታ ፊት ለፊት በሰሜንና በደቡብ ያሉት ክፍሎች የተቀደሱ ናቸው። የተቀደሱበት ምክንያት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡት ካህናት የተቀደሱ ቊርባኖችን የሚበሉባቸው ቦታዎች ስለ ሆኑ ነው፤ ቦታዎቹም የተቀደሱ በመሆናቸው የእህል ቊርባን፥ የኃጢአት ማስተስረያ ቊርባንና ለበደል የሚቀርብ መሥዋዕትን ያኖሩባቸዋል።
ሕግን በሚመለከት አከራካሪ ነገር በሚነሣበት ጊዜ፥ ደንቡ በሚያዝዘው መሠረት ካህናቱ ይወስኑላቸው፤ በሕጌና ሥርዓቴ መሠረት በዓሎቼን፥ እንዲሁም ዕለተ ሰንበትን በመቀደስ ይጠብቁ።
በዚያን ጊዜ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከሙ፥ በፊቱም በመቆም እንዲያገለግሉትና ሕዝቡን በእግዚአብሔር ስም እንዲባርኩ የሌዊን ነገድ በመለየት ሾመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የሌዊ ነገድ ትውልድ አገልግሎት ይኸው ነው።
እርስዋንም ጨርሶ ወዳልታረሰና ምንም ተክል ወዳልተተከለበት፥ ወንዙም ወደማይደርቅበት ሸለቆ ይዘዋት ወርደው በዚያ አንገትዋን በመቈልመም ይስበሩት፤