ዳዊትም ከሀዳድዔዜር አንድ ሺህ ሰባት መቶ ፈረሰኞችንና ኻያ ሺህ እግረኛ ወታደሮችን ማረከበት፤ ሠረገላ ለመሳብ የሚያገለግሉ አንድ መቶ ፈረሶችን አስቀርቶ፥ የቀሩትን ፈረሶች በሙሉ ቋንጃቸውን ቈርጦ ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆኑ አደረገ።
ዘዳግም 17:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያም ንጉሥ ለሠራዊቱ ብዙ ፈረሶች ያሉት መሆን የለበትም፤ እግዚአብሔር ሕዝቡ ወደ ግብጽ እንዳይመለሱ ስለ አዘዘ ፈረሶችን ለመግዛት ወደ እዚያ ሰዎችን አይላክ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ፤ ወይም ደግሞ የፈረሰኞችን ቍጥር ለመጨመር ሕዝቡን ወደ ግብጽ አይመልስ፤ እግዚአብሔር፣ “በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ” ብሏችኋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ፤ ወይም ደግሞ ፈረሰኞች ለማብዛት ሕዝቡን ወደ ግብጽ አይመልስ፤ ጌታ፥ ‘በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ’ ብሎአችኋልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእርሱ ፈረሶችን እንዳያበዛ፥ ሕዝቡንም ወደ ግብፅ እንዳይመልስ፤ እግዚአብሔር፦ በዚያች መንገድ መመለስን አትድገም ብሎአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ለእርሱ ፈረሶችን አያበዛም፤ እግዚአብሔር፦ በዚያ መንገድ ደግማችሁ አትመለሱም ብሎአችኋልና ፈረሶችን ለማብዛት ሕዝቡን ወደ ግብፅ አይመልስም። |
ዳዊትም ከሀዳድዔዜር አንድ ሺህ ሰባት መቶ ፈረሰኞችንና ኻያ ሺህ እግረኛ ወታደሮችን ማረከበት፤ ሠረገላ ለመሳብ የሚያገለግሉ አንድ መቶ ፈረሶችን አስቀርቶ፥ የቀሩትን ፈረሶች በሙሉ ቋንጃቸውን ቈርጦ ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆኑ አደረገ።
ከአቤሴሎም በኋላ ከዳዊትና ከሐጊት የተወለደ በሕይወት ያለ ተከታይ ልጅ አዶንያስ ነበር፤ እርሱም እጅግ መልከ ቀና ነበር፤ ዳዊት ስለማናቸውም ነገር ምክርና ተግሣጽ ሰጥቶት አያውቅም ነበር፤ ከዚህም የተነሣ አዶንያስ ለመንገሥ ፈለገ፤ ይህንንም ፍላጎቱን ለማሟላት ሠረገሎችን፥ ፈረሶችንና ኀምሳ ጋሻ ጃግሬዎችን አዘጋጀ።
ስለዚህ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት የሚቈርጡ ሰዎችን ወደ ሊባኖስ ላክልኝ፤ የእኔም ሰዎች ከእነርሱ ጋር አብረው እንዲሠሩ አደርጋለሁ፤ ለሰዎችህም አንተ የምትወስነውን ደመወዝ እከፍላለሁ፤ አንተ እንደምታውቀው የእኔ ሰዎች ስለ ዛፍ አቈራረጥ የአንተን ሰዎች ያኽል ዕውቀት የላቸውም።”
ንጉሥ ሰሎሞን ለሠረገሎቹና ለፈረሶቹ አራት ሺህ ጋጣዎች፥ እንዲሁም ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሰኞች ነበሩት፤ ከእነርሱም ከፊሉን በኢየሩሳሌም፥ የቀሩትም ደግሞ በሌሎች ልዩ ልዩ ከተሞች ተመድበው እንዲኖሩ አደረገ፤
የግብጽ ንጉሥ ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ቅርብ በሆነው በፍልስጥኤም የባሕር ጠረፍ በኩል ባለው መንገድ አልመራቸውም፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ሕዝቡ ከፊት ለፊታቸው ጦርነት እንደሚጠብቃቸው በሚያዩበት ጊዜ ሐሳባቸውን ለውጠው ወደ ግብጽ እንዳይመለሱ ነው።
ስለዚህ ይህን በማድረግ ፈንታ ወደ ቀይ ባሕር በሚያመራው በረሓ፥ ዘወርዋራ በሆነ መንገድ መራቸው፤ እስራኤላውያንም ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ሆነው ከግብጽ ወጡ።
ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “አይዞአችሁ አትፍሩ! ባላችሁበት ጸንታችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር እናንተን ለማዳን የሚያደርገውን ዛሬ ታያላችሁ፤ እነዚህን ዛሬ የምታዩአቸውን ግብጻውያን ዳግመኛ አታዩአቸውም።
ምድራቸው በብርና በወርቅ ስለ ተሞላች፥ ሀብታቸው ከመጠን በላይ ነው፤ አገራቸው በፈረሶች የተሞላች ሆናለች፤ ሠረገሎቻቸውም እጅግ ብዙ ናቸው።
“እናንተ ከስደት የተረፋችሁ የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ወደ እግዚአብሔር በላካችሁኝ ጊዜ እርሱ የሚያዘውን ሁሉ ንገረንና እንፈጽማለን ብላችሁ የማትፈጽሙትን ቃል በመግባታችሁ አደገኛ ስህተት ሠርታችኋል፤ አሁንም እግዚአብሔር ወደ ግብጽ አትሂዱ ብሎ ስለ ከለከለ እኔም ዛሬ ይህ ትእዛዝ እርግጠኛ መሆኑን በመግለጥ አስጠነቅቃችኋለሁ።
ነገር ግን የይሁዳ ንጉሥ ዐምፆ ፈረሶችንና ታላቅ ሠራዊት እንዲያመጡለት መልእክተኞችን ወደ ግብጽ ላከ፤ ታዲያ ይህ ዕቅዱ ይሳካለታልን? በዚህስ ሊያመልጥ ይችላልን? ውሉን የሚያፈርስ ከሆነ ከቅጣት ከቶ ያመልጣልን?
አሦር አያድነንም፥ በጦር ፈረሶችም አንታመንም፤ ከእንግዲህ ወዲህ በእጃችን የሠራነውን ጣዖት ሁሉ ‘አምላክ’ ብለን አንጠራም፤ አምላክ ሆይ! ወላጆቻቸው የሞቱባቸው በአንተ ምሕረትን ያገኛሉ።”
እግዚአብሔር ‘ዳግመኛ ተመልሰህ ወደዚያ አትሄድም’ ብሎ የተናገረ ቢሆንም እንኳ በመርከብ ተሳፍረህ ወደ ግብጽ እንድትመለስ ያደርጋል፤ በዚያም ራስህን ለጠላቶችህ ባሪያ አድርገህ መሸጥ ትፈልጋለህ፤ ነገር ግን ባሪያ አድርጎ ለመግዛት የሚፈልግህ እንኳ አታገኝም።”
እንዲህም ሲል ገለጠላቸው፤ “ንጉሣችሁ የሚያደርግባችሁ ነገር ይህ ነው፦ ልጆቻችሁን ወስዶ ሠረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ አንዳንዶቹም በሠረገሎቹም ፊት የሚሮጡ ያደርጋቸዋል፤