ዳንኤል 3:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ናቡከደነፆር በሲድራቅ፥ በሚሳቅና በአብደናጎ ላይ እጅግ ተቈጥቶ መልኩ ተለዋወጠ፤ ስለዚህ እሳቱ ከቀድሞው ይበልጥ በሰባት እጥፍ ከፍ ብሎ እንዲነድ ትእዛዝ ሰጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ናቡከደነፆር በሲድራቅ፣ በሚሳቅና በአብደናጎ እጅግ ተቈጣ፣ ፊቱም ተለወጠባቸው፤ የእቶኑ እሳትም ቀደም ሲል ከነበረው ሰባት ዕጥፍ ተደርጎ እንዲነድድ አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፥ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው፥ እርሱም ተናገረ፥ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ። |
ንጉሡም እጅግ ተቈጣና ግብዣውን ትቶ በመነሣት ከነበረበት ክፍል ወጥቶ ወደ ቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ ሄደ፤ ንጉሡ በዚህ ጥፋት ሊቀጣው የወሰነ መሆኑን ሃማን ተገንዝቦ ስለ ነበር ሕይወቱን ታተርፍለት ዘንድ ንግሥት አስቴርን ለመማጠን ወደ ኋላ ቀረ።
የመከራውንም ጽዋ ‘አጐንብሺና በጀርባሽ እንራመድብሽ’ ለሚሉና አንቺን ለሚያሠቃዩ ሰዎች በእጃቸው እሰጣለሁ፤ አንቺም እነርሱ ይራመዱብሽ ዘንድ ጀርባሽን እንደ መሬትና እንደ መንገድ አድርገሻል።”
ከዚህም በኋላ ዳንኤልን የከሰሱት ሰዎች ተይዘው እንዲመጡ ንጉሡ አዘዘ፤ እነርሱም ተይዘው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ እንዲጣሉ አደረገ፤ ገና ወደ ጒድጓዱ አዘቅት ሳይደርሱም አንበሶቹ ቦጫጨቋቸው፤ አጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።