Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 31:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በላባም ዘንድ እንደ ቀድሞው ተወዳጅ አለመሆኑን ተረዳ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የላባ አመለካከት ከቀድሞው የተለወጠበት መሆኑንም ያዕቆብ ተረዳ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እንደ ቀድሞው በላባ ተወዳጅ አለመሆኑን ያዕቆብም አየ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ያዕ​ቆ​ብም የላ​ባን ፊት አየ፤ እነ​ሆም፥ ከእ​ርሱ ጋር እንደ ዱሮው አል​ሆ​ነም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ያዕቆብም የላባን ፊት አየ እነሆም ከእርሱ ጋር እንደ ዱሮው አልሆነም።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 31:2
11 Referencias Cruzadas  

በዚያን ጊዜ ናቡከደነፆር በሲድራቅ፥ በሚሳቅና በአብደናጎ ላይ እጅግ ተቈጥቶ መልኩ ተለዋወጠ፤ ስለዚህ እሳቱ ከቀድሞው ይበልጥ በሰባት እጥፍ ከፍ ብሎ እንዲነድ ትእዛዝ ሰጠ።


ለቃየልና ለመሥዋዕቱ ግን ግምት አልሰጣቸውም፤ በዚህ ምክንያት ቃየል በጣም ተቈጣ፤ ፊቱም በቊጣ ተኮሳተረ፤


ስለዚህ ዮናታን ዳዊትን ጠርቶ ይህን ሁሉ ከነገረው በኋላ ወደ ሳኦል አቀረበው፤ ዳዊትም ከዚያ በፊት ያደርገው እንደ ነበር በንጉሡ ፊት እንደ ቀድሞው ማገልገሉን ቀጠለ።


ላባም “በልዩ መገለጥ እንደ ተረዳሁት በአንተ ምክንያት እግዚአብሔር የባረከኝ መሆኑን እንድገልጽልህ ፍቀድልኝ፤


በመካከላችሁ በመለሳለስና በቅምጥልነት በትውልዱም በመመካት የሚኖረው ሰው እንኳ ለወንድሙ፥ ዐቅፋው ለምትተኛው ሚስቱና ከጥፋት ለተረፉት ልጆቹ ከዚያ ምግብ ለመስጠት ይሰስታል።


አንድ ሰው ቀድሞ ጠላት ያልነበረውን አንድ ሰው የገደለው ሆን ብሎ በማሰብ ሳይሆን በአጋጣሚ አደጋ ምክንያት ሆኖ ከተገኘ አምልጦ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ በመግባት ሕይወቱን ያትርፍ።


ሙሴ ግን እንዲህ አለ፤ “እባክህ ጌታ ሆይ፥ ወደዚያ አትላከኝ፤ ቀድሞም ሆነ ወይም አሁን አንተ ከእኔ ጋር መነጋገር ከጀመርክበት ጊዜ አንሥቶ የመናገር ችሎታ የለኝም፤ እኔ አንደበቴ የሚኮላተፍና አጥርቼ ለመናገር የማልችል ነኝ።”


የላባ ወንዶች ልጆች “ያዕቆብ የአባታችንን ሀብት ወሰደ፤ ይህን ሁሉ ሀብት ያገኘው ከአባታችን ነው” እያሉ መናገራቸውን ያዕቆብ ሰማ።


በዚህን ጊዜ እግዚአብሔር ያዕቆብን “ወደ አባቶችህና ወደ ዘመዶችህ አገር ተመለስ፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ” አለው።


እንዲህም አላቸው፤ “አባታችሁ እንደ ቀድሞው ጊዜ እንደማይወደኝ ተረድቼአለሁ፤ ነገር ግን የአባቴ አምላክ ከእኔ ጋር አለ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios