ነገር ግን የደጋግ ሰዎች ቊጥር ኀምሳ መሆኑ ቀርቶ አርባ አምስት ቢሆን፥ አምስት ስለ ጐደለ ከተማይቱን በሙሉ ታጠፋለህን?” እግዚአብሔርም “አርባ አምስት ደጋግ ሰዎች ባገኝ ከተማይቱን አላጠፋም” አለ።
ዳንኤል 2:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ከቀሩት የባቢሎን ጠቢባን ጋር እንዳይገደሉ የሰማይ አምላክ ምሕረት እንዲያደርግላቸውና ምሥጢሩንም እንዲገልጥላቸው ይለምኑት ዘንድ አሳሰባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱና ጓደኞቹ ከቀሩት የባቢሎን ጠቢባን ጋራ እንዳይገደሉ፣ የሰማይ አምላክ ምሕረት ያደርግላቸውና ምስጢሩንም ይገልጥላቸው ዘንድ እንዲጸልዩ አሳሰባቸው። |
ነገር ግን የደጋግ ሰዎች ቊጥር ኀምሳ መሆኑ ቀርቶ አርባ አምስት ቢሆን፥ አምስት ስለ ጐደለ ከተማይቱን በሙሉ ታጠፋለህን?” እግዚአብሔርም “አርባ አምስት ደጋግ ሰዎች ባገኝ ከተማይቱን አላጠፋም” አለ።
የአሦር ንጉሥ ሕያው እግዚአብሔርን እንዲሰድብለት ከፍተኛ ባለሥልጣኑን ልኮአል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ስድብ ሰምቶ ተሳዳቢውን ይቀጣ ይሆናል፤ ስለዚህ ከሕዝባችን መካከል በሕይወት ስለሚተርፉት እባክህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ።”
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “ጥራኝ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ ከአሁን በፊት የማታውቃቸውን ተመርምሮ ሊደረሰባቸው የማይችሉትን ታላላቅ ነገሮች እገልጥልሃለሁ።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እስራኤላውያን ደግመው አንድ ጊዜ ይህን እንዲለምኑኝ አደርጋለሁ፤ ቊጥራቸውንም እንደ በጎች መንጋ አበዛዋለሁ።
የቀድሞ አባቶቼ አምላክ ሆይ! አመሰግንሃለሁ፤ ከፍ ከፍም አደርግሃለሁ፤ አንተ ጥበብንና ኀይልን ሰጥተኸኛል፤ ጸሎታችንንም ሰምተህ የንጉሡን ሕልም ገልጠህልናል።”
ጉቶው በመሬት ውስጥ እንዲቀር ትእዛዝ መሰጠቱ እግዚአብሔር በዓለም ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለው ካወቅህ በኋላ እንደገና ተመልሰህ የምትነግሥ መሆንህን ያመለክታል፤
ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እስቲ ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩትና ከእነርሱ አንዱ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ላይ ትቶ የጠፋውን አንዱን ለመፈለግ አይሄድምን?
ጴጥሮስን ካስያዘ በኋላ ወደ ወህኒ ቤት አስገባው፤ ከአይሁድ የፋሲካ በዓል በኋላ ለሕዝቡ እስኪያቀርበው ድረስ አራት አራት ሆነው እንዲጠብቁት ለአራት ጭፍሮች አስረከበው።
ወንድሞቼ ሆይ! ስለ እኔ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ በትግሌ እንድትረዱኝ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በመንፈስ ቅዱስ ፍቅር እለምናችኋለሁ።
እንግዲህ ይህ ሁሉ እንዲህ ከሆነ ጌታ እርሱን በማምለክ የሚኖሩትን ሰዎች ከፈተና እንደሚያድናቸው፥ ኃጢአተኞችንም እንዴት እንደሚቀጣና ለፍርድ ቀንም እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል ማለት ነው።
ከአንበሳና ድብ ያዳነኝ እግዚአብሔር ከዚህም ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል።” ሳኦልም “መልካም ነው! እንግዲህ ሂድ፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን!” ሲል መለሰለት።