Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማቴዎስ 18:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ደግሞም እላችኋለሁ፤ ከእናንተ ሁለቱ በምድር ላይ ማናቸውንም ነገር ለመለመን ተስማምተው ቢጸልዩ፥ በሰማይ ያለው አባቴ ይፈጽምላቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 “ደግሞም እውነት እላችኋለሁ፤ በምድር ላይ ሁለት ሆናችሁ ስለ ምንም ነገር በመስማማት ብትጠይቁ በሰማይ ያለው አባቴ ያደርግላችኋል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ደግሞም እውነት እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር ላይ በሚለምኑት በማንኛውም ነገር ሁሉ ቢስማሙ፥ በሰማያት ባለው አባቴ ይደረግላቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ደግሞ እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ፥ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ደግሞ እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ማቴዎስ 18:19
20 Referencias Cruzadas  

“ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ በር አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤


ስለዚህ በጸሎት ማናቸውንም ነገር ብትለምኑ፥ እንደ ተፈጸመላችሁ አድርጋችሁ እመኑ፤ የምትለምኑትም ሁሉ ይሰጣችኋል።


“በዚያን ቀን ከእኔ ምንም አትለምኑም፤ እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ አብን በስሜ ብትለምኑት ሁሉን ነገር ይሰጣችኋል።


ሌላው የምደሰትበት ምክንያት በእናንተ ጸሎትና በኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ርዳታ ነጻ እንደምወጣ ስለማውቅ ነው።


አምናችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ታገኛላችሁ።”


በእኔ ብትኖሩ ቃሌም በእናንተ ቢኖር የፈለጋችሁትን ብትለምኑ ታገኛላችሁ።


የእግዚአብሔርን ትእዛዞች የምንፈጽምና እርሱን ደስ የሚያሰኘውንም የምናደርግ ስለ ሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን።


ስለዚህ ጴጥሮስ በወህኒ ቤት ተይዞ ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር በጥብቅ ትጸልይ ነበር።


እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል።


እነዚህ ሁሉ ዘወትር ለጸሎት በአንድነት ይሰበሰቡ ነበር፤ ከእነርሱም ጋር አንዳንድ ሴቶችና የኢየሱስ እናት ማርያም፥ እንዲሁም የኢየሱስ ወንድሞች ነበሩ።


መባህን በመሠዊያው ፊት አስቀምጥና፥ ሄደህ በመጀመሪያ ከዚያ ከወንድም ጋር ታረቅ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሰህ መባህን አቅርብ።


እኛ ግን በመጸለይና የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር እንተጋለን።”


ጳውሎስ ይህን ራእይ ካየ በኋላ ወዲያውኑ ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ፈለግን፤ ይህም የሆነው ለመቄዶንያ ሰዎችም ወንጌልን እንድናስተምር ጌታ እንደ ጠራን ስለ ተረዳን ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios