Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዳንኤል 4:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ጉቶው በመሬት ውስጥ እንዲቀር ትእዛዝ መሰጠቱ እግዚአብሔር በዓለም ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለው ካወቅህ በኋላ እንደገና ተመልሰህ የምትነግሥ መሆንህን ያመለክታል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 የዛፉ ጕቶ ከነሥሩ እንዲቀር መታዘዙ፣ ሥልጣን ከሰማይ መሆኑን ስታውቅ መንግሥትህ እንደሚመለስልህ ያመለክታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 የዛፉንም ጉቶ ይተዉት ዘንድ ማዘዙ፥ ሥልጣን ከሰማያት እንደ ሆነ ካወቅህ በኋላ መንግሥትህ ይቆይልሃል።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 4:26
13 Referencias Cruzadas  

እነርሱም ከቀሩት የባቢሎን ጠቢባን ጋር እንዳይገደሉ የሰማይ አምላክ ምሕረት እንዲያደርግላቸውና ምሥጢሩንም እንዲገልጥላቸው ይለምኑት ዘንድ አሳሰባቸው።


በዚያኑ ሌሊት ምሥጢሩ ለዳንኤል በራእይ ተገለጠለት፤ ስለዚህ የሰማይን አምላክ እንዲህ ሲል አመሰገነ፦


ንጉሥ ሆይ! አንተ ከሁሉ የምትበልጥ ንጉሠ ነገሥት ነህ፤ የሰማይ አምላክ መንግሥትንና ኀይልን፤ ሥልጣንና ክብርን ሰጥቶሃል።


ጒቶውን ግን ከብረትና ከነሐስ በተሠራ ሰንሰለት ዙሪያውን አስራችሁ በመሬት ውስጥ ተዉት፤ በለምለም ሣር መካከል እንዳለ በሜዳው ላይ እንዲቀር አድርጉት። “ ‘በሰማይም ጠል ይረስርስ፤ በመስክ ከአራዊት ጋር ሣር እየበላ ይኑር።


ንጉሥ ሆይ! አንተ እየተመለከትከው አንድ የሚጠብቅ ቅዱስ ከሰማይ ወርዶ እንዲህ አለ፦ ‘ዛፉን ቈርጣችሁ አጥፉ፤ ጒቶውን ግን ከብረትና ከነሐስ በተሠራ ሰንሰለት ዙሪያውን አስራችሁ በምድር ውስጥ ተዉት፤ በመስኩ ላይ በሣር መካከል ይቈይ፤ በሰማይም ጠል ይረስርስ፤ እስከ ሰባት ዓመት ድረስ ኑሮው ከዱር አራዊት ጋር ይሁን።’


ንግግሩን ገና ሳይጨርስ እንዲህ የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ፤ “ንጉሥ ናቡከደነፆር ሆይ! የተላለፈብህን ውሳኔ ስማ! እነሆ፥ መንግሥትህ ከአንተ ተወስዳለች፤


“እነሆ፥ እኔ ናቡከደነፆር ለሰማይ ንጉሥ ምስጋና፥ ክብርና ውዳሴ አቀርባለሁ፤ እርሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው፤ መንገዱም ፍትሓዊ ነው፤ በትዕቢት የሚመሩትንም ሁሉ ማዋረድ ይችላል።”


ነገር ግን ትዕቢተኛ፥ እልኸኛና ጨካኝ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ክብሩንና ማዕርጉን ተገፎ ከዙፋኑ ወረደ፤


ከሕዝብ መካከል ተባረረ፤ አእምሮውም ተለውጦ እንደ እንስሳ ሆነ፤ እንደ በሬም ሣር እየበላ ከሜዳ አህዮች ጋር ሆኖ ለመኖር ተገደደ፤ መጠለያ አጥቶ ሰውነቱ በሰማይ ጠል ረሰረሰ፤ ይህም የሆነው ልዑል እግዚአብሔር በመንግሥታት ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለውና መንግሥትን ሁሉ ለፈለገው መስጠት እንደሚችል እስከሚረዳበት ጊዜ ድረስ ነበር።


ደቀ መዛሙርቱ ይህን ባዩ ጊዜ፥ “ይህች የበለስ ዛፍ በአንድ አፍታ እንዴት ደረቀች!” በማለት ተገረሙ።


እኔ ግን “በፍጹም አትማሉ” እላችኋለሁ። ሰማይ የእግዚአብሔር ዙፋን ስለ ሆነች፥ በሰማይም ቢሆን፥


ተነሥቼ ወደ አባቴ ልሂድና፦ አባባ፥ በእግዚአብሔርና በአንተ ፊት በድያለሁ፤


ልጁም ‘አባባ፥ በእግዚአብሔርና በአንተ ፊት በድያለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅህ ልባል አይገባኝም’ አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos