ዳንኤል 11:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተንኰል የሰላም ውል በመደራደር ሌሎችን ያታልላል፤ የእርሱ ተከታዮች ጥቂቶች ቢሆኑም እየበረታ ይሄዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱ ጋራ ስምምነት ከተደረገ በኋላ የማታለል ሥራውን ይሠራል፤ ከጥቂት ሰዎች ጋራ ለሥልጣን ይበቃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም ጋር ከተወዳጀ በኋላ በተንኰል ያደርጋል፥ ከጥቂትም ሕዝብ ጋር ወጥቶ ይበረታል። |
እጅግ ሀብታም የሆነ አንድ ክፍለ ሀገር በድንገት ይይዛል፤ ከቀድሞ አባቶቹ አንዱ እንኳ ያላደረገውን ነገር ሁሉ ያደርጋል፤ በጦርነት የማረከውንም ዕቃና ንብረት ሁሉ ለጭፍሮቹ ያከፋፍላል፤ በምሽጎች ላይ አደጋ ለመጣል ዕቅድ ያወጣል፤ ነገር ግን ለጥቂት ጊዜ ነው።
ይህም ንጉሥ እጅግ ብርቱ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ በራሱ ኀይል አይደለም፤ እጅግ አሠቃቂ የሆነ ጥፋት ይፈጽማል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል፤ በኃያላን ሰዎችና በተቀደሱት ሕዝብ ላይ ጥፋትን ያስከትላል።
እጅግም ተንኰለኛ ስለ ሆነ በማታለል ይበለጽጋል፤ ራሱንም ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ብዙ ሰዎችን ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ ይገድላል፤ የልዑላንን ልዑል እንኳ ይፈታተናል፤ በመጨረሻም እርሱ ራሱ ይጠፋል፤ የሚጠፋውም በሰው ኀይል አይደለም።
ስለዚህ በበደል፥ በክፋት፥ በሥሥት፥ በተንኰል፥ በምቀኝነት፥ በነፍሰገዳይነት፥ በጥል፥ በአታላይነት፥ በክፉ ምኞት ሁሉ የተሞሉ፥ እንዲሁም ሐሜተኞች ናቸው፤
እባብ ሔዋንን በተንኰሉ እንዳሳታት ምናልባት የእናንተም ሐሳብ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ያላችሁን ቅንና ንጹሕ የሆነ ታማኝነት ትተዋላችሁ ብዬ እፈራለሁ።