ዳንኤል 11:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሶርያ ንጉሥ ወንዶች ልጆች ለጦርነት በመዘጋጀት ታላቅ ሠራዊት ያደራጃሉ፤ ከእነርሱ አንዱ ጠራርጎ እንደሚወስድ እንደ ኀይለኛ ጐርፍ ሆኖ በማለፍ በጠላት ምሽግ ላይ አደጋ ይጥላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንዶች ልጆቹም ለጦርነት ይዘጋጃሉ፤ እስከ ጠላት ምሽግ ደርሶ የሚዋጋና ሊቋቋሙት እንደማይቻል ጐርፍ የሚጠራርግ ታላቅ ሰራዊት ያሰባስባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጆቹም ይዋጋሉ፥ ብዙ ሠራዊትንና ሕዝብን ይሰበስባል፥ እርሱም ይመጣል፥ ይጐርፍማል፥ ያልፍማል፥ ተመልሶም እስከ አምባው ድረስ ይዋጋል። |
ወዲያውኑ የእርስዋ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ይነግሣል፤ ከሶርያ ንጉሥ ሠራዊት ጋር ጦርነት ይገጥማል፤ ምሽጋቸውንም ሰብሮ በመግባት ድል ይነሣቸዋል።
ከስድሳ ሁለት ሳምንት በኋላ መሲሑ ያለ ፍትሕ ይገደላል፤ የሚገደለውም ለራሱ አይደለም፤ የሚመጣው መሪ ወታደሮች ቤተ መቅደሱንና ከተማይቱን ይደመስሳሉ፤ መጨረሻውም እንደ ጐርፍ ይመጣል፤ ውድመት ስለ ታወጀ ጦርነት እስከ መጨረሻ ይቀጥላል።