Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዳንኤል 11:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ወንዶች ልጆቹም ለጦርነት ይዘጋጃሉ፤ እስከ ጠላት ምሽግ ደርሶ የሚዋጋና ሊቋቋሙት እንደማይቻል ጐርፍ የሚጠራርግ ታላቅ ሰራዊት ያሰባስባሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “የሶርያ ንጉሥ ወንዶች ልጆች ለጦርነት በመዘጋጀት ታላቅ ሠራዊት ያደራጃሉ፤ ከእነርሱ አንዱ ጠራርጎ እንደሚወስድ እንደ ኀይለኛ ጐርፍ ሆኖ በማለፍ በጠላት ምሽግ ላይ አደጋ ይጥላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ልጆቹም ይዋጋሉ፥ ብዙ ሠራዊትንና ሕዝብን ይሰበስባል፥ እርሱም ይመጣል፥ ይጐርፍማል፥ ያልፍማል፥ ተመልሶም እስከ አምባው ድረስ ይዋጋል።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 11:10
10 Referencias Cruzadas  

“ከዘመዶቿ አንዱ ስፍራዋን ሊይዝ ይነሣል፤ የሰሜንን ንጉሥ ሰራዊት ይወጋል፤ ምሽጎቹንም ጥሶ ይገባል፤ ከእነርሱም ጋራ ተዋግቶ ድል ያደርጋል።


ከስድሳ ሁለቱ ሱባዔ በኋላ መሲሑ ይገደላል፤ ምንም አይቀረውም። የሚመጣው አለቃ ሰዎችም፣ ከተማውንና ቤተ መቅደሱን ይደመስሳሉ። ፍጻሜውም እንደ ጐርፍ ይመጣል፤ ጦርነት እስከ መጨረሻው ይቀጥላል፤ ጥፋትም ታውጇል።


ባሕር በባቢሎን ላይ ይወጣል፤ ሞገዱም እየተመመ ይሸፍናታል።


ከንጉሥ ማእድ ዐብረውት ሲበሉ የነበሩት ሊያጠፉት ያሤራሉ፤ ሰራዊቱም ይደመሰሳል፤ ብዙዎቹም በጦርነት ይወድቃሉ።


ከፊቱ የሚቆመውን ታላቅ ሰራዊት፣ የቃል ኪዳኑንም አለቃ ሳይቀር ይደመስሳል።


ከፍ ብሎ የተመሸገውን ቅጥርህን ዝቅ ያደርገዋል፤ ወደ ታች ያወርደዋል፤ ወደ ምድር አውርዶም ትቢያ ላይ ይጥለዋል።


የሰሜኑም ንጉሥ፣ የደቡቡን ንጉሥ ግዛት ይወርራል፤ ነገር ግን አፈግፍጎ ወደ ገዛ አገሩ ይመለሳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios