Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዳንኤል 11:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ወዲያውኑ የእርስዋ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ይነግሣል፤ ከሶርያ ንጉሥ ሠራዊት ጋር ጦርነት ይገጥማል፤ ምሽጋቸውንም ሰብሮ በመግባት ድል ይነሣቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ከዘመዶቿ አንዱ ስፍራዋን ሊይዝ ይነሣል፤ የሰሜንን ንጉሥ ሰራዊት ይወጋል፤ ምሽጎቹንም ጥሶ ይገባል፤ ከእነርሱም ጋራ ተዋግቶ ድል ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ነገር ግን ከሥርዋ ቍጥቋጥ አንዱ በስፍራው ይነሣል፥ ወደ ሠራዊቱም ይመጣል፥ ወደ ሰሜንም ንጉሥ አምባ ይገባል፥ በላያቸውም ያደርጋል፥ ያሸንፍማል።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 11:7
14 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ግን ‘አንተ ሞኝ፥ ዛሬ በዚህች ሌሊት ነፍስህ ከአንተ ትወሰዳለች፤ ታዲያ ይህ ያከማቸኸው ሀብት ሁሉ ለማን ይሆናል?’ አለው።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።


እርሱ መሐላውን በመናቅ ቃል ኪዳኑን ስላፈረሰና እጁን ከሰጠ በኋላ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ስላደረገ አያመልጥም።”


አንተ ተክለሃቸዋል፤ እነርሱም ሥር ሰደዋል፤ አድገውም ፍሬ ያፈራሉ፤ በአፋቸው ያከብሩሃል፤ ልባቸው ግን ከአንተ የራቀ ነው።


ግንድ እንደሚያቈጠቊጥና ከስሩም ቅርንጫፍ እንደሚያበቅል እንዲሁም ከእሴይ (ከዳዊት ንጉሣዊ) ዘር አንድ ንጉሥ ይወጣል።


ስለዚህ እግዚአብሔር በአንድ ቀን እንደ ራስና እንደ ጅራት እንደ ዘንባባውና እንደ ቅርንጫፉ የሚቈጠሩትን ከእስራኤል ይቈርጣል።


ዕድሜውም በቶሎ ይቀጭ፤ ሥራውንም ሌላ ሰው ይውሰድበት።


አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።


“ለተቈረጠ የዛፍ ጒቶ እንኳ ተስፋ አለው፤ እንደ ገና ሊያቈጠቊጥና ቅርንጫፎችም ሊያበቅል ይችላል።


ከጥቂት ዓመቶች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ከሶርያ ንጉሥ ጋር የወዳጅነት ቃል ኪዳን ይመሠርታል፤ ሴት ልጁንም ለሶርያ ንጉሥ ይድርለታል፤ ነገር ግን እርስዋ ኀይልዋን ለማጠናከር ካለመቻልዋ የተነሣ የንጉሡ ኀይል ስለማይጸና የወዳጅነቱም ውል ጸንቶ አይኖርም፤ ስለዚህም እርስዋ ከደጋፊዎችዋ፥ ከልጆችዋና ከአገልጋዮችዋ ጋር ትገደላለች።


“ጊዜው ሲደርስ የግብጽ ንጉሥ በሶርያ ንጉሥ ላይ አደጋ ይጥልበታል፤ ሆኖም የሶርያ ንጉሥ በሠረገሎች፥ በፈረሶችና በመርከቦች በመጠቀም በብርቱ ጦርነት ይቋቋመዋል፤ እንደ ጐርፍ ውሃ በመጠራረግ ብዙ አገሮችን ይወራል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios