ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን የመሰለ ነገር በሕዝቦች መካከል ተሰምቶ እንደ ሆነ ጠይቁ፤ የተለዩ የእስራኤል ሕዝብ በጣም አጸያፊ የሆነ ነገር አድርገዋል።
አሞጽ 5:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በእናንተ ላይ እኔ የማወርደውን ይህን ሙሾ አድምጡ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለ እናንተ የምደረድረውን ይህን የሙሾ ቃል ስሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ቤት ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ ለሙሾ የማነሣውን ይህን ቃል ስሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል ቤት ሆይ! በእናንተ ላይ ለሙሾ የማነሣውን ይህን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በእናንተ ላይ ለሙሾ የማነሣውን ይህን ቃል ስሙ። |
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን የመሰለ ነገር በሕዝቦች መካከል ተሰምቶ እንደ ሆነ ጠይቁ፤ የተለዩ የእስራኤል ሕዝብ በጣም አጸያፊ የሆነ ነገር አድርገዋል።
“የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ፥ ጠጒራችሁን ተላጭታችሁ በመጣል እዘኑ፤ ዛፎች በሌሉባቸው ኰረብቶች ራስ ላይ ሙሾ አውጡ፤ እኔ እግዚአብሔር ተቈጥቻለሁ፤ ሕዝቤንም ከፊቴ አሽቀንጥሬ ጥያለሁ።
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ሁሉም ወና ስለ ሆኑና በእነርሱም ላይ የሚዘዋወርባቸው ስለሌለ፥ ስለ ተራራዎች አዝናለሁ፤ ስለ ሜዳዎችም አለቅሳለሁ፤ የከብቶች ድምፅ ዳግመኛ አይሰማም፤ የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ሁሉ ሸሽተው ጠፍተዋል።”
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “እናንተ ሴቶች፥ እግዚአብሔር የሚለውን አድምጡ፤ ቃሉንም ለመቀበል የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ እንዴት ማልቀስ እንደሚገባቸው ሴቶች ልጆቻችሁን አስተምሩ፤ ሙሾ የማውጣትንም ዘዴ ለወዳጆቻችሁ አስጠኑ።
ከወይን ተክሉ ግንድ እሳት ወጣ፤ ቅርንጫፎቹንና ፍሬውን ሁሉ እሳት በላው፤ ቅርንጫፎቹ ዳግመኛ ብርቱ አይሆኑምና በትረ መንግሥት መሆንም አይችሉም። እንግዲህ በመደጋገም የሚደረደረው ሙሾ ይህ ነው። እርሱም ለለቅሶ ያገለግላል።
እንዲህም እያሉ ስለ አንቺ ሙሾ ያወጣሉ፤ ‘በባሕር ጠረፍ ያሉ አገሮችን ያሸበራችሁ፥ በባሕር ላይ ኀያል የነበርሽ ዝነኛይቱ ከተማ ሆይ! እንዴት ከባሕር ጠፋሽ?
“የሰው ልጅ ሆይ! የጢሮስ ንጉሥ ስለሚገጥመው መጥፎ ዕድል ሙሾ አውጣ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለውንም እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ‘በጥበብ የተሞላህና እጅግ መልከ ቀና በመሆንህ የፍጹምነት ምሳሌ ነበርክ።
“የሰው ልጅ ሆይ! ለግብጽ ንጉሥ አልቅስለትና በብርቱም በማስጠንቀቅ እኔ የምሰጥህን እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ‘አንተ በአሕዛብ መካከል ስትኖር ራስህን እንደ አንበሳ አድርገህ ቈጥረሃል፤ ነገር ግን አንተ በባሕር ውስጥ እንደሚገላበጥ አስፈሪ የባሕር አውሬ ነህ፤ በእግሮችህ እያንቦጫረቅህ ውሃውን ታደፈርሳለህ።
እንደ ባሳን ቅልብ ላሞች ሰውነታችሁን ያወፈራችሁ የሰማርያ ሴቶች ሆይ! ይህን ቃል አድምጡ! እናንተ ደካሞችን ታዋርዳላችሁ፤ ድኾችን ትጨቊናላችሁ፤ ባሎቻችሁ ሁልጊዜ የሚያሰክር መጠጥ እንዲያቀርቡላችሁ ትጠይቃላችሁ።
ስለዚህ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በየመንገዱና በየአደባባዩ ዋይታና ለቅሶ ይሰማል፤ ገበሬዎች እንኳ ለለቅሶ ይጠራሉ፤ ከሙሾ አውጪዎችም ጋር ስለ ሞቱ ሰዎች ያለቅሳሉ፤
‘አሺማ’ ተብላ በምትጠራ በሰማርያ ሴት አምላክ የሚምሉ ‘በዳን አምላክ’ ወይም ‘በቤርሳቤህ አምላክ’ እያሉ የሚምሉ ሁሉ ይወድቃሉ፤ ከወደቁበትም ፈጽሞ መነሣት አይችሉም።”
በዚያን ቀን ሰዎች ያፌዙባችኋል፤ እንዲህም እያሉ የምፀት ሙሾ ያወርዱላችኋል፦ “እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል! እግዚአብሔር የሕዝባችንን ንብረት ወሰደብን፤ ርስታችንንም ለማራኪዎቻችን አከፋፈለ።”