ሐዋርያት ሥራ 7:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ያዕቆብ ወደ ግብጽ ሄደ፤ እርሱና አባቶቻችን እዚያ ሞቱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ ወደ ግብጽ ወረደ፤ እርሱም አባቶቻችንም በዚያ ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ወደ ግብጽ ወረደ፤ እርሱም ሞተ፤ አባቶቻችንም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ያዕቆብም ወደ ግብፅ ወረደ፥ እርሱም አባቶቻችንም ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ወደ ግብፅ ወረደ እርሱም ሞተ አባቶቻችንም፤ |
አባቶቼ በተቀበሩበት መቃብር መቀበር ስለምፈልግ በምሞትበት ጊዜ ከግብጽ አገር ወስደህ፥ እነርሱ በተቀበሩበት ስፍራ ቅበረኝ።” ዮሴፍም “እሺ እንዳልከኝ አደርጋለሁ” አለው።
ዮሴፍ “እግዚአብሔር ታድጎአችሁ በምትወጡበት ጊዜ ዐፅሜን ከዚህች ምድር ይዛችሁ እንድትወጡ” በማለት ተናግሮ ስለ ነበረ አስከሬኑን እንዲወስዱ እስራኤላውያንን በመሐላ ቃል ኪዳን ባስገባቸው መሠረት ሙሴ የዮሴፍን አስከሬን ይዞ ሄደ።
የቀድሞ አባቶቻችን እንዴት ወደ ግብጽ እንደ ወረዱና እኛም በግብጽ ለብዙ ዓመቶች እንዴት እንደ ኖርን ታውቃለህ፤ ግብጻውያን የቀድሞ አባቶቻችንም ሆነ እኛን በብርቱ አሠቃይተዋል፤
የቀድሞ አባቶችህ ወደ ግብጽ በወረዱ ጊዜ ብዛታቸው ሰባ ብቻ ነበር፤ አሁን ግን እግዚአብሔር አምላክህ የአንተን ቊጥር ብዛት እንደ ሰማይ ከዋክብት አድርጎታል።
ከዚያ በኋላ በእግዚአብሔር አምላክህ ፊት ይህን መግለጫ ስጥ፦ ‘አባቴ ከቦታ ወደ ቦታ በመዞር የሚኖር ሶርያዊ ነበር፤ ጥቂት ቤተሰብ ይዞ ወደ ግብጽ በመውረድ መጻተኛ ሆኖ ኖረ፤ ጥቂት የነበረው ታላቅ፥ ኀያል፥ ብዙ ሕዝብ ሆነ።
የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ያወጡት የዮሴፍ ዐፅም በሴኬም ተቀበረ፤ ይህም ምድር ያዕቆብ የሼኬም አባት ከሆነው ከሐሞር ልጆች በአንድ መቶ ጥሬ ብር የገዛው ነበር፤ ምድሩም የሚገኘው በዮሴፍ ዘሮች የርስት ድርሻ ክልል ውስጥ ነው።
ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁ፤ ለዔሳውም የኤዶምን ኮረብታማ አገር ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤ ነገር ግን ያዕቆብና ልጆቹ ወደ ግብጽ ወረዱ፤