Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 13:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ዮሴፍ “እግዚአብሔር ታድጎአችሁ በምትወጡበት ጊዜ ዐፅሜን ከዚህች ምድር ይዛችሁ እንድትወጡ” በማለት ተናግሮ ስለ ነበረ አስከሬኑን እንዲወስዱ እስራኤላውያንን በመሐላ ቃል ኪዳን ባስገባቸው መሠረት ሙሴ የዮሴፍን አስከሬን ይዞ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ዮሴፍ፣ “እግዚአብሔር በርግጥ ይጐበኛችኋል፤ በዚያ ጊዜም ዐፅሜን ይዛችሁ ከዚች ምድር መውጣት አለባችሁ” ብሎ የእስራኤልን ልጆች አስምሏቸው ስለ ነበር ሙሴ የዮሴፍን ዐፅም ይዞ ወጣ። እግዚአብሔር ሕዝቡን ዙሪያ በሆነው በምድረ በዳው መንገድ ወደ ቀይ ባሕር መራቸው፤ እስራኤላውያንም ለጦርነት ዝግጁ ሆነው ከግብጽ ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ሙሴም የዮሴፍን አጥንቶች ከእርሱ ጋር ወሰደ፥ “በእርግጥ እግዚአብሔር ይጎበኛችኋል፥ አጥንቶቼንም ከዚህ ከእናንተ ጋር ውሰዱት” ብሎ የእስራኤልን ልጆች አምሎአቸው ነበርና።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሙሴም የዮ​ሴ​ፍን ዐጽም ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መጐ​ብ​ኘ​ትን በጐ​በ​ኛ​ችሁ ጊዜ ዐጽ​ሜን ውሰዱ፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ከዚህ አውጡ” ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አም​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ዮሴፍም፥ “እግዚአብሔር ሳይጎበኛችሁ አይቀርም፤ አፅሜን ከዚህ ከእናንተ ጋር ታወጣላችሁ” ብሎ የእስራኤልን ልጆች አምሎአቸው ነበርና ሙሴ የእርሱን አፅም ከእርሱ ጋር ወሰደ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 13:19
9 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፥ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፤ ወደ ቀድሞ አባቶቻችሁም ምድር ይመልሳችኋል፤


ሕዝቡም አመኑ፤ እግዚአብሔር ወደ እነርሱ መጥቶ እንደ ጐበኛቸውና የደረሰባቸውንም የግፍ ጭቈና ማየቱን በሰሙ ጊዜ ተንበርክከው ሰገዱ።


ጐረቤቶችዋና ዘመዶችዋ ሁሉ ጌታ ታላቅ ምሕረቱን እንዳደረገላት ሰምተው ከእርስዋ ጋር ተደሰቱ።


ሁሉንም ፍርሀት ይዞአቸው፥ “ታላቅ ነቢይ ከመካከላችን ተነሥቶአል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ሊያድን መጥቶአል፤” እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።


ስለዚህ ያዕቆብ ወደ ግብጽ ሄደ፤ እርሱና አባቶቻችን እዚያ ሞቱ።


ዐጽማቸው ወደ ሴኬም ተወስዶ አብርሃም በሴኬም ከኤሞር ልጆች በገንዘቡ በገዛው መቃብር ተቀበረ።


ዮሴፍም የሚሞትበት ጊዜ ሲቃረብ እስራኤላውያን ከግብጽ እንደሚወጡ የተናገረው ስለ ዐፅሙም ምን ማድረግ እንዳለባቸው ትእዛዝ የሰጠው በእምነት ነው።


የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ያወጡት የዮሴፍ ዐፅም በሴኬም ተቀበረ፤ ይህም ምድር ያዕቆብ የሼኬም አባት ከሆነው ከሐሞር ልጆች በአንድ መቶ ጥሬ ብር የገዛው ነበር፤ ምድሩም የሚገኘው በዮሴፍ ዘሮች የርስት ድርሻ ክልል ውስጥ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos