ሐዋርያት ሥራ 6:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ ግን በመጸለይና የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር እንተጋለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ ግን በጸሎትና በቃሉ አገልግሎት እንተጋለን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማስተማር እንተጋለን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን።” |
እነዚህ ሁሉ ዘወትር ለጸሎት በአንድነት ይሰበሰቡ ነበር፤ ከእነርሱም ጋር አንዳንድ ሴቶችና የኢየሱስ እናት ማርያም፥ እንዲሁም የኢየሱስ ወንድሞች ነበሩ።
ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ሰዎች እንዲሁም ፊቴን እንኳ አይተውት ስለማያውቁ ሰዎች ሁሉ ምን ያኽል ብርቱ ትግል እንደማደርግ ልታውቁ እወዳለሁ።
የእናንተ ወገን የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ኤጳፍራም ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በመንፈሳዊ ሕይወት በማደግ ጸንታችሁ እንድትቆሙና የእግዚአብሔርንም ፈቃድ በሙሉ እንድትፈጽሙ እርሱ ስለ እናንተ በጸሎቱ ዘወትር ይጸልያል።