ሐዋርያት ሥራ 16:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እኩለ ሌሊት ገደማ ጳውሎስና ሲላስ በጸሎትና በመዝሙር እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ ሌሎችም እስረኞች ያዳምጡአቸው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኩለ ሌሊት አካባቢ ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩና እየዘመሩ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ነበር፤ ሌሎቹ እስረኞችም ያዳምጧቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፤ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንፈቀ ሌሊትም ጳውሎስና ሲላስ ጸለዩ፤ እግዚአብሔርንም በዜማ አመሰገኑት፤ እስረኞቹም ይሰሙአቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር |
በችግር ጊዜ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ሌሊቱን ሙሉ ያለ ዕረፍት እጆቼን ዘርግቼ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ይሁን እንጂ ለመጽናናት አልቻልኩም።
እናንተ ግን ደስ ይላችኋል፤ በተቀደሰ በዓል ምሽት እንደምትዘምሩት ትዘምራላችሁ፤ የእስራኤል አምባ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዋሽንት እየነፉ እንደሚዘምሩት ሰዎች ትደሰታላችሁ።
ሊቀ ካህናት ኢያሱ ሆይ! ይህን ስማ፤ እናንተም ከእርሱ ጋር በክህነት የምታገለግሉና ወደ ፊት ለሚሆነው መልካም ነገር ምልክት የምትሆኑ ይህን አድምጡ፤ ‘ቅርንጫፍ’ ተብሎ የሚጠራውን አገልጋዬን ወደ ፊት እልካለሁ።
ከዚህ በኋላ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያን ሰዎች ሁሉ ጋር ሆነው ከጉባኤው መካከል ጥቂት ሰዎችን መርጠው ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ለመላክ ወሰኑ፤ ስለዚህ በወንድሞች መካከል በመሪነት መልካም ዝና የነበራቸውን በርሳባስ የተባለውን ይሁዳንና ሲላስን መረጡ።
አሳዳሪዎችዋ ጥቅም የሚያገኙበት ተስፋ እንደ ተቋረጠባቸው ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ያዙአቸው፤ እየጐተቱም ወደ አደባባይ ወሰዱአቸውና በሹሞች ፊት አቀረቡአቸው።
ለእግዚአብሔር በእምነት በምታቀርቡት መሥዋዕትና አገልግሎት ላይ የእኔም ሕይወት ተጨማሪ መሥዋዕት ሆኖ ቢቀርብ እንኳ ደስ ይለኛል፤ እናንተም የደስታዬ ተካፋዮች ትሆናላችሁ።
አሁን ስለ እናንተ በምቀበለው መከራ ደስ ይለኛል፤ አካሉ ስለ ሆነችው ስለ ቤተ ክርስቲያንም ከክርስቶስ መከራ ከመካፈል የጐደለብኝን በሥጋዬ አሟላለሁ።
ኢየሱስ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር በኖረበት ጊዜ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል አምላክ በታላቅ ጩኸትና በብዙ እንባ ጸሎትንና ልመናን አቀረበ፤ በትሕትና ራሱን ታዛዥ በማድረጉ እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማው።