እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ወደ ላይ ወደ መኖሪያህ በወጣህ ጊዜ ምርኮን ይዘህ ሄድክ፤ ከዐመፀኞች እንኳ ሳይቀር ከሰዎች ሁሉ ምርኮን ተቀበልክ።
ሐዋርያት ሥራ 1:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ካለ በኋላ እነርሱ እያዩት ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ደመናም ተቀብሎ ከዐይናቸው ሰወረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ካለ በኋላ እያዩት ወደ ላይ ዐረገ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰወረችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም እየነገራቸው ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ተቀበለችው፤ እነርሱም ወደ እርሱ እያዩ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ከዐይናቸውም ተሰወረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። |
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ወደ ላይ ወደ መኖሪያህ በወጣህ ጊዜ ምርኮን ይዘህ ሄድክ፤ ከዐመፀኞች እንኳ ሳይቀር ከሰዎች ሁሉ ምርኮን ተቀበልክ።
እግዚአብሔርም ሙሴን “እኔ ግዙፍ በሆነ ደመና ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ስለዚህም ሕዝቡ እኔ ከአንተ ጋር ስነጋገር በመስማት ከአሁን ጀምሮ አንተ የምትለውን ሁሉ ያምናሉ።” ሙሴም ሕዝቡ የሰጠውን መልስ ወደ እግዚአብሔር አቀረበ፤
ስለ ግብጽ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል የሚከተለው ነው፦ እነሆ፥ እግዚአብሔር በደመና ሆኖ በፍጥነት ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጻውያን ጣዖቶች በፊቱ ይናወጣሉ፤ የግብጽ ሕዝብም በፍርሃት ይርበደበዳሉ።
“እናንተ የገሊላ ሰዎች፥ ስለምን ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ቆማችኋል? ይህ ወደ ሰማይ ሲያርግ ያያችሁት ኢየሱስ፥ ወደ ሰማይ ሲያርግ ባያችሁት ዐይነት ተመልሶ ይመጣል” አሉአቸው።
ወደ ሰማይ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ የሠራውን ነው፤ ወደ ሰማይ ያረገውም ለመረጣቸው ሐዋርያት ትእዛዙን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ከሰጣቸው በኋላ ነው፤
ከዚህ በኋላ እኛ በሕይወት የምንገኘው ጌታን በአየር ላይ ለመገናኘት ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ ለዘለዓለምም ከጌታ ጋር እንሆናለን።
የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም እግዚአብሔር፦ “ሰው ሆኖ ተገለጠ፤ እውነተኛነቱ በመንፈስ ታወቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ ለሕዝቦች ሁሉ ተሰበከ፥ በዓለም ያሉ ሰዎች አመኑበት፥ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ” የሚል ነው።
እነሆ በደመና ይመጣል፤ የወጉት ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ሰው ሁሉ ያየዋል፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ምክንያት ያለቅሳሉ፤ ይህ ነገር እውነት ነው፤ አሜን።
ከዚህ በኋላ ሁለቱ ነቢያት “ወደዚህ ወደ ላይ ውጡ!” የሚል ታላቅ ድምፅ ከሰማይ ሰሙ፤ ጠላቶቻቸው እየተመለከቱአቸውም በደመና ወደ ሰማይ ወጡ።
እነርሱ ድንግሎች ስለ ሆኑ ከሴቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ አልረከሱም፤ በጉ ወደሚሄድበትም ሁሉ ይከተሉታል። እነርሱ ለእግዚአብሔርና ለበጉ ከሰዎች መካከል እንደ በኲራት የቀረቡ ናቸው።