2 ጢሞቴዎስ 3:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ፥ ለገንዘብ የሚስገበገቡ፥ ትምክሕተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ ውለታቢሶች፥ ቅድስና የሌላቸው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች ራሳቸውን የሚወድዱ ይሆናሉ፤ ገንዘብን የሚወድዱ፣ ትምክሕተኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎች እንዲህ ይሆናሉና፤ ራሳቸውን የሚወዱ፥ ገንዘብን ወዳጆች፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፤ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ |
አንተ ብርቱ ሰው፥ በእግዚአብሔር ወገኖች ላይ ክፉ ነገር በማድረግ የእግዚአብሔር ፍቅር ዘለዓለማዊ መሆኑን እያወቅህስ ስለምን ዘወትር ትመካለህ?
መጥረቢያ እንጨት በሚቈርጥበት በባለቤቱ ላይ መነሣት ይችላልን? መጋዝስ በሚሰነጥቅበት ሰው ላይ መነሣት ይችላልን? እንዲሁም በትር በሚይዘው ሰው ላይ ኀይል አይኖረውም።
“የሶርያ ንጉሥ የፈለገውን ሁሉ ይፈጽማል፤ ራሱንም ከአማልክት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ከአማልክት ሁሉ በላይ ባለው አምላክ ላይ ከዚህ በፊት ተሰምቶ የማይታወቅ የስድብ ቃል ይናገራል፤ የታቀደው ሁሉ መደረግ ስላለበት የእግዚአብሔር የቊጣው ቀን እስኪደርስ ድረስ ይሳካለታል።
በልዑል እግዚአብሔር ላይ በመታበይ ይናገራል፤ የልዑል እግዚአብሔርንም ቅዱሳን ያስጨንቃል፤ የተቀደሱ በዓላትንና ሕጉን ለመለወጥ ያቅዳል፤ ቅዱሳኑም ለሦስት ዓመት ተኩል በእርሱ ሥልጣን ሥር ይሆናሉ።
‘ያ ሰው አባቱን [ወይም እናቱን] ማክበር አያስፈልገውም’ ትላላችሁ፤ ስለዚህ ወጋችሁን ለማጥበቅ ብላችሁ የእግዚአብሔርን ሕግ ታፈርሳላችሁ፤
እናንተ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ! መልካም ነገርም አድርጉላቸው፤ ‘ብድራችን ይመለስልናል’ ብላችሁ ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ይህን ብታደርጉ ዋጋችሁ ትልቅ ይሆናል፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጆችም ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለውለታ ቢሶችና ለክፉዎች እንኳ ሳይቀር ቸር ነው።
ከዚህ በፊት ቴዎዳስ የሚባል ሰው ‘እኔ ትልቅ ሰው ነኝ’ ብሎ ተነሥቶ ነበር፤ አራት መቶ የሚያኽሉም ሰዎች ከእርሱ ጋር ተባብረው ነበር። ነገር ግን እርሱ ተገደለ፤ ተከታዮቹ ተበታተኑ፤ ዓላማውም እንዳልነበረ ሆነ።
እናንተ አሕዛብ እንደ ቅርንጫፍ ተቈርጠው በወደቁት አይሁድ ላይ አትታበዩ፤ ብትታበዩ ግን እናንተ ቅርንጫፎች ብቻ በመሆናችሁ ሥሩ እናንተን ይሸከማችኋል እንጂ እናንተ ሥሩን የማትሸከሙ መሆናችሁን አስታውሱ።
በሕይወት ያሉት ሁሉ ለእነርሱ ለሞተውና ከሞትም ለተነሣው እንዲኖሩ እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ ለራሳቸው ሲሉ እንዳይኖሩ ክርስቶስ ለሁሉም ሞተ።
ስለዚህ በእናንተ የሚገኙትን የምድራዊ ሕይወት ምኞቶች ሁሉ ግደሉ፤ እነርሱም “ዝሙት፥ ርኲሰት፥ ፍትወት፥ ክፉ ምኞት፥ ጣዖት ማምለክ የሆነ መጐምጀት” ናቸው።
ይህ የዐመፅ ሰው አማልክት ተብለው ከሚመለኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ያደርጋል፤ “እግዚአብሔር ነኝ” እያለም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንኳ ለመቀመጥ ይደፍራል።
ከእነርሱ መካከል ሄሜኔዎስና እስክንድር ይገኛሉ፤ እነርሱ በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ከመናገር መቈጠብን እንዲማሩ ለሰይጣን አሳልፌ ሰጥቼአቸዋለሁ።
እንዲሁም ሕግ የተሠራው ለደጋግ ሰዎች እንዳልሆነ እናውቃለን፤ ሕግ የተሠራው ለዐመፀኞችና ለወንጀለኞች፥ እግዚአብሔርን ለማያመልኩና ለኃጢአተኞች፥ ቅድስና ለሌላቸውና መንፈሳዊ ነገርን ለሚንቁ፥ አባትንና እናትን ለሚገድሉና ለነፍሰ ገዳዮች፥
በትዕቢት የተወጠረና ምንም የማያውቅ ነው፤ ነገር ግን ስለ ቃላት የመከራከርና የመጨቃጨቅ ክፉ ምኞት አድሮበታል፤ ይህም የሚያስከትለው ቅንአትን፥ ጠብን፥ ስድብን፥ መጥፎ ጥርጣሬን፥
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።
በተለይም እነዚያን ርኩስ የሆነውን የሥጋ ፍትወታቸውን የሚከተሉትንና የእግዚአብሔርን ሥልጣን የሚንቁትን ለፍርድ ጠብቆ ያቈያቸዋል። እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ደፋሮችና ትዕቢተኞች ስለ ሆኑ የሰማይ ሥልጣናትን ሲሳደቡ አይፈሩም።
እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ግን ለማስተዋል ያቃታቸውን ነገር ይሳደባሉ፤ እነርሱ ለመጠመድና ለመገደል እንደ ተወለዱ፥ በተፈጥሮ ስሜት እንደሚኖሩና አእምሮ እንደሌላቸው እንስሶች ናቸው፤ እንስሶች እንደሚጠፉ እነርሱም ፈጽመው ይጠፋሉ።
በስሕተት ከሚኖሩት ሰዎች መካከል አምልጠው ከመጡ ገና ብዙ ያልቈዩትን ሰዎች ከንቱ የሆነ የዕብሪት ቃል በመናገር፥ በሥጋዊ ፍትወትና በሴሰኛነት በማባበል ያታልሉአቸዋል።
እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ፍርድ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል!
እነዚህ ሰዎች ሁልጊዜ የሚያጒረመርሙና በምንም ነገር የማይደሰቱ ናቸው፤ የራሳቸውን ክፉ ምኞት የሚከተሉ ናቸው፤ አፋቸው በትዕቢት ቃል የተሞላ ነው፤ የራሳቸውን ጥቅም በመፈለግ ሰውን ይለማመጣሉ።
ከዚህ በኋላ አንድ አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ ዐሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፤ በቀንዶቹም ላይ ዐሥር ዘውዶች ነበሩ፤ በራሶቹም ላይ የስድብ ስሞች ነበሩ።
እያንዳንዱ አርባ አምስት ኪሎ ግራም ያኽል የሚመዝን በረዶ ከሰማይ በሰዎች ላይ ወረደ፤ መቅሠፍቱ እጅግ አሠቃቂ ስለ ነበረ ሰዎች በበረዶው መቅሠፍት ምክንያት እግዚአብሔርን ተሳደቡ።
ሰዎች በታላቅ ግለት ተቃጠሉ፤ በእነዚህ መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፤ ንስሓ አልገቡም፤ እርሱንም አላከበሩም።