ባለሟሎቹ ሁሉ በእርሱ በኩል አለፉ፤ የዳዊት ክብር ዘበኞች የነበሩት ከሪታውያንና ፈሊታውያን፥ እንዲሁም ከጋት የመጡ ስድስት መቶ ጌታውያን በንጉሡ ፊት አለፉ፤
2 ሳሙኤል 8:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮዳሄ ልጅ በናያ የዳዊት ክብር ዘብ አዛዥ ነበር፤ የዳዊትም ልጆች አማካሪዎቹ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮዳሄ ልጅ በናያስ የከሊታውያንና የፈሊታውያን አዛዥ ነበር፤ የዳዊት ወንዶች ልጆች ደግሞ አማካሪዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮዳሔ ልጅ በናያ የከሪታውያንና የፈሊታውያን አለቃ ሲሆን፥ የዳዊት ወንዶች ልጆች ደግሞ አማካሪዎች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮዳሄ ልጅ በናያስም አማካሪ ነበረ፤ ከሊታውያንና፥ ፊሊታውያን፥ የዳዊትም ልጆች የፍርድ ቤት አለቆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮዳሄ ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ፥ የዳዊትም ልጆች አማካሪዎች ነበሩ። |
ባለሟሎቹ ሁሉ በእርሱ በኩል አለፉ፤ የዳዊት ክብር ዘበኞች የነበሩት ከሪታውያንና ፈሊታውያን፥ እንዲሁም ከጋት የመጡ ስድስት መቶ ጌታውያን በንጉሡ ፊት አለፉ፤
ስለዚህ የኢዮአብ ወታደሮች፥ የንጉሡ የክብር ዘበኞችና ሌሎች ወታደሮችም ከአቢሳ ጋር ከኢየሩሳሌም ወጥተው የቢክሪን ልጅ ሼባዕን በመከታተል አሳደዱት።
ስለዚህ ካህኑ ሳዶቅ፥ ነቢዩ ናታን፥ የዮዳሄ ልጅ በናያና የንጉሡ ክብር ዘበኞች ሰሎሞንን ዳዊት በሚቀመጥባት በቅሎ ላይ በማስቀመጥ ወደ ግዮን ምንጭ ወረዱ፤
ንጉሡም እርሱን ያጅቡት ዘንድ ካህኑን ሳዶቅን፥ ነቢዩን ናታንን፥ የዮዳሄን ልጅ በናያንና የቤተ መንግሥቱን ክብር ዘበኞች ልኮአል፤ እነርሱም ንጉሡ በሚቀመጥባት በቅሎ ላይ እንዲቀመጥ አድርገውታል።
ነገር ግን በሰባተኛው ዓመት ካህኑ ዮዳሄ ለንጉሡ ክብር ዘቦችና ለቤተ መንግሥቱ ጠባቂዎች ሁሉ ኀላፊዎች ወደሆኑት የጦር መኰንኖች ሁሉ ልኮ ወደ ቤተ መቅደስ እንዲመጡ አስጠራቸው፤ በዚያም ሊያደርገው ያቀደውን ይስማሙበት ዘንድ በመሐላ እንዲያረጋግጡለት አደረገ፤ ከዚያም በኋላ የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን አሳያቸውና፥
በቃብጽኤል ምድር የዮዳሄ ልጅ በናያ ዝነኛ ወታደር ነበር፤ እርሱ ሁለት የታወቁ ሞአባውያን ጦረኞችን ከመግደሉም ሌላ ብዙ የጀግንነት ሥራ ፈጽሞአል፤ አንድ ጊዜ በምድር ላይ ዐመዳይ በወረደበት ቀን ወደ አንድ ዋሻ ወርዶ አንበሳ ገደለ፤
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘በፍልስጥኤማውያን ላይ ኀይሌን እጠቀማለሁ፤ ብሪታውያንን እፈጃለሁ፤ በባሕር ጠረፍ የቀሩትንም አጠፋለሁ።
እናንተ በባሕር ዳር የምትኖሩ ከሪታውያን ማለት ፍልስጥኤማውያን ወዮላችሁ! የእግዚአብሔር ፍርድ በእናንተ ላይ ደርሷል፤ የፍልስጥኤም ምድር ለሆንሽው ከነዓን ወዮልሽ አንድ እንኳ ነዋሪ እንዳይኖርብሽ አድርጌ አጠፋሻለሁ።