2 ሳሙኤል 6:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት ከበፍታ የተሠራ ሽርጥ በወገቡ ዙሪያ ታጥቆ እግዚአብሔርን በማክበር በሙሉ ኀይሉ ያሸበሽብ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም የበፍታ ኤፉድ በወገቡ ታጥቆ በሙሉ ኀይሉ በእግዚአብሔር ፊት ይጨፍር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም የበፍታ ኤፉድ በወገቡ ታጥቆ በሙሉ ኀይሉ በጌታ ፊት ይጨፍር ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በእግዚአብሔር ፊት በገና ይደረድር ነበር፤ ዳዊትም ለዐይን የሚያንጸባርቅ የሐር ቀሚስ ለብሶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በሙሉ ኃይሉ በእግዚአብሔር ፊት ይዘፍን ነበር፥ ዳዊትም የበፍታ ኤፉድ ለብሶ ነበር። |
ከዚያም በኋላ ዳዊት ቤተሰቡን ሰላም ለማለት ወደ ቤት ገባ፤ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ልትቀበለው ወጣችና “የእስራኤል ንጉሥ ዛሬ ትልቅ ስም አግኝቶአል! በመኳንንቱ ገረዶች ፊት እንደ ቅሌታም ሽማግሌ እርቃኑን ገልጦአል!” አለችው።
ዳዊት ከጥሩ በፍታ የተሠራ መጐናጸፊያና ኤፉድ ለብሶ ነበር፤ እንዲሁም መዘምራኑ በሙሉ፥ የመዘምራኑ መሪ ከናንያና የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ሌዋውያን ከጥሩ በፍታ የተሠራ ልብስ ለብሰው ነበር።
ለእኔም ብቻ የተለያችሁ ቅዱሳን ሕዝብ ትሆናላችሁ፤ እንደ ካህናትም ሆናችሁ ታገለግሉኛላችሁ፤’ ለእስራኤላውያን የምትነግራቸው ቃል ይኸው ነው።”
ዮፍታሔ በምጽጳ ወዳለው ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ሴት ልጁ አታሞ ይዛ እየጨፈረች ልትቀበለው ወጣች፤ ያለ እርስዋም ሌላ ወንድ ወይም ሴት ልጅ አልነበረውም።
ተጠባበቁ፤ በበዓሉ ዕለት የሴሎ ልጃገረዶች ለመጨፈር ሲመጡ እናንተም ከወይኑ ተክል ውስጥ ውጡ፤ እያንዳንዳችሁ ከእነዚያ ልጃገረዶች መካከል እየጠለፋችሁ ሚስት አድርጋችሁ ውሰዱ፤ ወደ ብንያም ግዛትም ይዛችኋቸው ሂዱ።
ሳሙኤል ግን ገና በልጅነቱ ከበፍታ የተሠራ ሸሚዝ ለብሶ በእግዚአብሔር ፊት ያገለግል ነበር፤ ይህም ቃል በዕብራይስጡ ካህኑ ለሚለብሰው ልብስ ወይም በደረቱ ላይ ስለሚያደርገው ነገር መጠሪያ ነው።
እርሱንም ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ወደ መሠዊያዬ እንዲወጣ፥ እጣን እንዲያጥን፥ በፊቴ ኤፉድ እንዲለብስ፥ የእኔ ካህን ይሆን ዘንድ መረጥሁት፤ ለቀድሞ አባትህ ልጆችም የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡትን የሚቃጠል መሥዋዕት ሰጠኋቸው።
ስለዚህም ሳኦል ዶይቅን “አንተው ግደላቸው!” አለው፤ ኤዶማዊው ዶይቅም ተነሥቶ ሁሉንም ገደለ፤ በዚያኑ ቀን የፈጃቸው ኤፉድ የሚለብሱ ካህናት ብዛት ሰማኒያ አምስት ነበር፤