2 ሳሙኤል 22:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሲኦል ገመድ ተበተበኝ፤ የሞት ወጥመድም ተጠመደብኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሲኦል ገመድ ተጠመጠመብኝ፤ የሞት ወጥመድም ተጋረጠብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሲኦል ገመድ ተበተበኝ፤ የሞትም ወጥመድ ተጋረጠብኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሞት ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድም ደረሰብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሲኦል ጣር ከበበኝ፥ የሞት ወጥመድ ደረሰብኝ። |
“እግዚአብሔር ሆይ! ተጨንቄ ሳለሁ ወደ አንተ ተጣራሁ፤ አንተም መለስክልኝ፤ ርዳታህን ለማግኘት ጥልቅ ከሆነው ከሙታን ዓለም ወደ አንተ ጮኽኩ፤ አንተም ሰማኸኝ።