2 ሳሙኤል 19:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባርዚላይ ሰማኒያ ዓመት የሞላው ሽማግሌ ሰው ነበር፤ በጣም ሀብታም ከመሆኑም የተነሣ ንጉሥ ዳዊት በማሕናይም በነበረበት ጊዜ ይኸው ባርዚላይ ምግብ ያቀርብለት ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ቤርዜሊ በዕድሜ የገፋ የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነበር፤ እጅግ ባለጠጋ ስለ ነበረም ንጉሡ በመሃናይም ሳለ የሚመገበውን አምጥቶለት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ገለዓዳዊው ባርዚላይ ከሮገሊም ወረደ፤ ንጉሡን ለመሸኘትም አብሮት ዮርዳኖስን ተሻገረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤርዜሊም እጅግ ያረጀ የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነበረ፤ እጅግም ትልቅ ሰው ነበረና ንጉሡ በመናሄም ሳለ ይቀልበው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤርዜሊም እጅግ ያረጀ የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነበረ፥ እጅግም ትልቅ ሰው ነበረና ንጉሡ በመሃናይም ሳለ ይቀልበው ነበር። |
ምናሔም ገንዘቡን የሰበሰበው የእስራኤል ከበርቴዎች እያንዳንዳቸው ኀምሳ ጥሬ ብር አዋጥተው እንዲሰጡ በማስገደድ ነበር። በዚህም ዐይነት ቲግላት ፐሌሴር በሰላም ወደ አገሩ ተመልሶ ሄደ።
በሀብትም በኩል ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎችና አምስት መቶ አህዮች ነበሩት፤ እንዲሁም እጅግ ብዙ አገልጋዮች ነበሩት፤ በምሥራቅ አገር ካሉት ሰዎች ሁሉ እርሱን የሚያኽል ሀብታምና ታላቅ ሰው አልነበረም።
በዚያም ቤተሰቡ ከካሌብ ጐሣ የሆነ ናባል ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም የማዖን ተወላጅ ሲሆን በቀርሜሎስ ከተማ አጠገብ የእርሻ መሬት ነበረው፤ ታላቅ ባለጸጋ ከመሆኑም የተነሣ ሦስት ሺህ በጎችና አንድ ሺህ ፍየሎች ነበሩት፤ ሚስቱ አቢጌልም እጅግ የተዋበች አስተዋይ ሴት ስትሆን እርሱ ግን መልካም ጠባይ የጐደለው ባለጌ ሰው ነበር። ናባል በቀርሜሎስ በጎቹን ያሸልት ነበር፤