ከዚህ በኋላ ዳዊትና ሠራዊቱ ባመሩበት መንገድ ተጓዙ፤ ሺምዒም በኮረብታው ጥግ እነርሱን ተከትሎ እየሄደ በመራገም ድንጋይና ዐፈር በእነርሱ ላይ ይወረውር ነበር።
2 ሳሙኤል 19:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጸሩያ ልጅ አቢሳም “እግዚአብሔር ቀብቶ ያነገሠውን ስለተሳደበ ሺምዒ በሞት መቀጣት ይገባዋል” ሲል ተናገረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የጽሩያ ልጅ አቢሳ፣ “ሳሚ በእግዚአብሔር የተቀባውን የረገመ ስለ ሆነ፣ መሞት አይገባውምን?” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ አገልጋይህ ኃጢአት መሥራቴን አውቃለሁና፤ እነሆ፥ ዛሬ ግን ጌታዬ ንጉሡን ለመቀበል ከዮሴፍ ቤት ሁሉ የመጀመሪያ ሆኜ መጥቻለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሶርህያ ልጅ አቢሳ ግን፥ “ሳሚ እግዚአብሔር የቀባውን ሰድቦአልና እንግዲህ ሞት የተገባው አይደለምን?” ብሎ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጽሩያ ልጅ አቢሳ ግን፦ ሳሚ እግዚአብሔር የቀባውን ሰድቦአልና ሞት የተገባው አይደለምን? አለ። |
ከዚህ በኋላ ዳዊትና ሠራዊቱ ባመሩበት መንገድ ተጓዙ፤ ሺምዒም በኮረብታው ጥግ እነርሱን ተከትሎ እየሄደ በመራገም ድንጋይና ዐፈር በእነርሱ ላይ ይወረውር ነበር።
በዚህ ጊዜ የጸሩያ ልጅ አቢሳ ንጉሡን “ንጉሥ ሆይ! ይህ የሞተ ውሻ ጌታዬን ንጉሡን እንዴት ይራገማል? እኔ ሄጄ ራሱን ልቊረጠው!” አለው።
ስለዚህም ተከታዮቹን “እግዚአብሔር ቀብቶ ባነገሠው በጌታዬ ላይ እጄን ከማንሣት እግዚአብሔር ይጠብቀኝ! እርሱ እግዚአብሔር የመረጠው ንጉሥ ስለ ሆነ እኔ በእርሱ ላይ ምንም ዐይነት ጒዳት ላደርስበት አይገባኝም!” አላቸው።