La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 17:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህም ጋር “እንግዲህ ዛሬ ሌሊት በበረሓ ውስጥ በሚገኘው በወንዙ መሻገሪያ ላይ እንዳያድር በፍጥነት መልእክተኛ ልካችሁ ለዳዊት ንገሩት! ነገር ግን እርሱና ተከታዮቹ ተይዘው እንዳይገደሉ በፍጥነት የዮርዳኖስን ወንዝ ይሻገሩ!” አላቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሁንም በፍጥነት ላኩና፣ ‘በምድረ በዳው ባለው የወንዙ መሻገሪያ እንዳታድር፤ ሳትዘገይ ፈጥነህ መሻገር አለብህ፤ አለዚያ ግን ንጉሡና ዐብሮት ያለው ሕዝብ በሙሉ ትዋጣላችሁ’ ብላችሁ ለዳዊት ንገሩት።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አሁንም በፍጥነት ላኩና፥ ‘ንጉሡና ከእርሱ ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ እንዳትዋጡ፥ በዚህች ሌሊት በምድረ በዳ መሻገሪያ እንዳታድር ሳትዘገይ ተሻገር፤’ ብላችሁ ለዳዊት ንገሩት፤ አላቸው።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሁን እን​ግ​ዲህ ንጉ​ሡና ከእ​ርሱ ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ እን​ዳ​ይ​ዋጡ፥ ሳት​ዘ​ገይ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገር እንጂ በዚ​ህች ሌሊት በም​ድረ በዳ ውስጥ በሜ​ዳው አት​ደር ብለው ለዳ​ዊት ይነ​ግ​ሩት ዘንድ ፈጥ​ና​ችሁ ላኩ” አላ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አሁን እንግዲህ ንጉሡና ከእርሱ ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ እንዳይዋጡ፥ ፈጥናችሁ፦ ሳትዘገይ ተሻገር እንጂ በዚህች ሌሊት በምድረ በዳ መሻገሪያ አትደር ብላችሁ ለዳዊት ንገሩት አላቸው።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 17:16
14 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም ዳዊት ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም ለሚገኙት መኳንንቱ ሁሉ “ከአቤሴሎም እጅ ማምለጥ ከፈለግን በፍጥነት ከዚህ ሸሽተን እንውጣ! እንግዲህ ፍጠኑ! አለበለዚያ በፍጥነት መጥቶ ድል ይመታናል፤ በከተማይቱ ያገኘውንም ሁሉ ይገድላል!” አላቸው።


እኔም ከአንተ ወሬ እስከማገኝ ድረስ በበረሓው ውስጥ በሚገኘው በወንዙ መሸጋገሪያ ላይ እጠባበቃለሁ።”


ካህናቱ ሳዶቅና አብያታርም በዚያው ይገኛሉ፤ በቤተ መንግሥት የምትሰማውን ነገር ሁሉ ለእነርሱ ትነግራቸዋለህ፤


“ይኸዋ የልባችን ምኞት ደረሰ!” ብለው እንዲያስቡና ወይም “እኛ አሸነፍነው!” እንዲሉ አታድርግ።


ከዚህ ከደረሰብኝ ዐውሎ ነፋስና ሞገድ መጠለያ ስፍራ ለማግኘት ፈጥኜ በሄድኩ ነበር።


ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ያጠቁኛል፤ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ የሚያሳድዱኝ ብዙዎች ናቸው።


እግዚአብሔር ከሰማይ ልኮ ያድነኛል፤ የሚያስጨንቁኝንም ያዋርዳቸዋል፤ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ፍቅሩንና ታማኝነቱን ይገልጣል።


ይህ የሚጠፋው የማይጠፋውን ይህም የሚሞተው የማይሞተውን በሚለብስበት ጊዜ “ሞት በድል ተዋጠ!” ተብሎ የተጻፈው ይፈጸማል።


በዚህ እንደ ምድራዊ ድንኳን በሆነው ሥጋችን ውስጥ ስንኖር ከብደን እንቃትታለን፤ የምንቃትተውም ሞት በሕይወት እንዲለወጥ ሰማያዊውን አካል በበለጠ እንድንለብስ ነው እንጂ ከዚህ ከምድራዊ ሥጋችን ለመለየት በመፈለግ አይደለም።


እዚያ ዝም ብለህ አትቁም! ፈጠን በል!” ሲል ጮኸበት፤ ልጁም ፍላጻውን አንሥቶ ወደ ጌታው ተመለሰ፤