Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ሳሙኤል 17:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 አሁን እን​ግ​ዲህ ንጉ​ሡና ከእ​ርሱ ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ እን​ዳ​ይ​ዋጡ፥ ሳት​ዘ​ገይ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገር እንጂ በዚ​ህች ሌሊት በም​ድረ በዳ ውስጥ በሜ​ዳው አት​ደር ብለው ለዳ​ዊት ይነ​ግ​ሩት ዘንድ ፈጥ​ና​ችሁ ላኩ” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 አሁንም በፍጥነት ላኩና፣ ‘በምድረ በዳው ባለው የወንዙ መሻገሪያ እንዳታድር፤ ሳትዘገይ ፈጥነህ መሻገር አለብህ፤ አለዚያ ግን ንጉሡና ዐብሮት ያለው ሕዝብ በሙሉ ትዋጣላችሁ’ ብላችሁ ለዳዊት ንገሩት።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 አሁንም በፍጥነት ላኩና፥ ‘ንጉሡና ከእርሱ ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ እንዳትዋጡ፥ በዚህች ሌሊት በምድረ በዳ መሻገሪያ እንዳታድር ሳትዘገይ ተሻገር፤’ ብላችሁ ለዳዊት ንገሩት፤ አላቸው።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህም ጋር “እንግዲህ ዛሬ ሌሊት በበረሓ ውስጥ በሚገኘው በወንዙ መሻገሪያ ላይ እንዳያድር በፍጥነት መልእክተኛ ልካችሁ ለዳዊት ንገሩት! ነገር ግን እርሱና ተከታዮቹ ተይዘው እንዳይገደሉ በፍጥነት የዮርዳኖስን ወንዝ ይሻገሩ!” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 አሁን እንግዲህ ንጉሡና ከእርሱ ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ እንዳይዋጡ፥ ፈጥናችሁ፦ ሳትዘገይ ተሻገር እንጂ በዚህች ሌሊት በምድረ በዳ መሻገሪያ አትደር ብላችሁ ለዳዊት ንገሩት አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 17:16
14 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያሉ​ትን አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ሁሉ፥ “ተነሡ እን​ሽሽ፤ ከአ​ቤ​ሴ​ሎም እጅ የም​ን​ድ​ን​በት የለ​ን​ምና፤ ፈጥኖ እን​ዳ​ይ​ዘን፥ ክፉም እን​ዳ​ያ​መ​ጣ​ብን፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም በሰ​ልፍ ስለት እን​ዳ​ይ​መታ ፈጥ​ና​ችሁ እን​ሂድ” አላ​ቸው።


እዩ፤ እኔም እነሆ፥ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ወሬ እስ​ኪ​መ​ጣ​ልኝ ድረስ በም​ድረ በዳው ውስጥ በሜ​ዳው እቈ​ያ​ለሁ” አለው።


እነሆ፥ ካህ​ናቱ ሳዶ​ቅና አብ​ያ​ታ​ርም በዚያ ከአ​ንተ ጋር ናቸው። ከን​ጉሡ ቤትም የም​ት​ሰ​ማ​ውን ነገር ሁሉ ለካ​ህ​ናቱ ለሳ​ዶ​ቅና ለአ​ብ​ያ​ታር ንገ​ራ​ቸው።


አም​ላኬ ሆይ፥ ሕይ​ወ​ቴን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ እን​ባ​ዬ​ንም እንደ ትእ​ዛ​ዝህ በፊ​ትህ አኖ​ርሁ።


ወደ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ወደ​ሚ​ረ​ዳኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጮ​ኻ​ለሁ።


ኀጥ​ኣን ከማ​ኅ​ፀን ጀም​ረው ተለዩ፤ ከሆ​ድም ጀም​ረው ሳቱ፥ ሐሰ​ት​ንም ተና​ገሩ።


ይህ የሚ​ፈ​ር​ሰው የማ​ይ​ፈ​ር​ሰ​ውን በለ​በሰ ጊዜ፥ የሚ​ሞ​ተ​ውም የማ​ይ​ሞ​ተ​ውን በለ​በሰ ጊዜ፤ “ሞት በመ​ሸ​ነፍ ተዋጠ” ተብሎ የተ​ጻ​ፈው ያን​ጊዜ ይፈ​ጸ​ማል።


በዚህ ቤት ውስጥ ሳለ​ንም ከከ​ባ​ድ​ነቱ የተ​ነሣ እጅግ እና​ዝ​ና​ለን፤ ነገር ግን ሟች በሕ​ይ​ወት ይዋጥ ዘንድ ሌላ ልን​ለ​ብስ እንጂ ልን​ገ​ፈፍ አን​ወ​ድም።


ዮና​ታ​ንም ደግሞ፥ “ቶሎ ፍጠን፤ አት​ቈይ” ብሎ ወደ ብላ​ቴ​ናው ጮኸ፤ የዮ​ና​ታ​ንም ብላ​ቴና ፍላ​ጻ​ዎ​ቹን ሰብ​ስቦ ወደ ጌታው መጣ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos