የሠራዊቱ አዛዥ ናቡዛርዳን ሊቀ ካህናቱን ሤራያን በማዕርግ የእርሱ ምክትል የሆነውን ካህኑን ሶፎንያስና ሦስቱን የቤተ መቅደስ ዘበኞች እስረኛ አድርጎ ወሰዳቸው፤
የክብር ዘበኞቹ አዛዥም ሊቀ ካህኑን ሠራያን፣ በማዕርግ ከርሱ ቀጥሎ ያለውን ካህኑን ሶፎንያስንና ሦስቱን የበር ጠባቂዎች እስረኛ አድርጎ ወሰዳቸው።
የሠራዊቱ አዛዥ ናቡዛርዳን ሊቀ ካህናቱን ሤራያን በማዕረግ የእርሱ ምክትል የሆነውን ካህኑን ሶፎንያስና ሦስቱን የቤተ መቅደስ ዘበኞች እስረኛ አድርጎ ወሰዳቸው፤
የአበዛዎችም አለቃ ታላቁን ካህን ሠራያን ሁለተኛውንም ካህን ሶፎንያስን ሦስቱንም በረኞች ማርኮ ወሰደ።
የዘበኞቹም አለቃ ታላቁን ካህን ሠራያን፥ ሁለተኛውንም ካህን ሶፎንያስን፥ ሦስቱንም በረኞች ወሰደ።
ከዚህም በኋላ ኢዮስያስ ሊቀ ካህናቱን ሒልቅያን፥ ረዳቶቹ የሆኑትን ካህናትና የቤተ መቅደሱን መግቢያ በር ዘብ የሚጠብቁ ተረኞችን ጠርቶ ለባዓልና አሼራ ተብላ ለምትጠራው ሴት አምላክ፥ እንዲሁም ለከዋክብት ማምለኪያ ያገለግሉ የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ ከቤተ መቅደስ ያወጡ ዘንድ አዘዛቸው፤ ንጉሡም እነዚያን ዕቃዎች ሁሉ ከኢየሩሳሌም ውጪ ባለው በቄድሮን ሸለቆ በእሳት አቃጥሎ ዐመዱን ወደ ቤትኤል ወሰደው፤
ዐዛርያስ ሤራያን ወለደ፤ ሤራያም ኢዮጼዴቅን ወለደ።
ከብዙ ጊዜ በኋላ አርጤክስስ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት በሆነበት ዘመን፥ ዕዝራ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው በዚያ ይኖር ነበር፤ የእርሱም የቀድሞ አባቶች የትውልድ ሐረግ እስከ ታላቁ ሊቀ ካህናት አሮን ድረስ ሲቈጠር እንደሚከተለው ነው፦ ዕዝራ የሠራያ ልጅ ሲሆን፥ ሠራያ የዐዛርያ ልጅ፥ ዐዛርያ የሒልቂያ ልጅ፥ ሒልቂያ የሻሉም ልጅ፥
የቤተ መቅደሱ አለቃ የሆነው የኢሜር ልጅ ፖሽሑር ይህን ስናገር በሰማ ጊዜ፥
የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ የመልክያን ልጅ ፓሽሑርንና የመዕሤያን ልጅ ካህኑን ሶፎንያስን ወደ እኔ ልኮ እንዲህ ሲል አስጠየቀኝ፦
አንተና መኳንንትህ ከወረርሽኝ፥ ከጦርነትና ከራብ የሚተርፉትንም ሕዝብ በሙሉ በንጉሥ ናቡከደነፆርና ሊገድሉህ በሚፈልጉህ ጠላቶችህ እንድትማረኩ አደርጋለሁ፤ እርሱም ምሕረት ወይም ርኅራኄ በማሳየት አንድ ሰው እንኳ አይተውልህም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’ ”
ሶፎንያስ ደብዳቤውን ለእኔ ለኤርምያስ አነበበልኝ፤
“የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና መኳንንቱን ሁሉ ሕይወታቸውን ማጥፋት ለሚፈልጉ ጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ አሳልፌ የምሰጣችሁም በእናንተ ላይ አደጋ የመጣል ተግባሩን ለገታው ለባቢሎናውያን ሠራዊት ነው።
ከዚያም ሁሉ ጋር የሠራዊቱ አዛዥ ናቡዛርዳን ሊቀ ካህናቱን ሠራያን፥ በማዕርግ የእርሱ ምክትል የሆነውን ካህኑን ሶፎንያስንና ሌሎችንም ሦስት የቤተ መቅደስ በር ጠባቂዎችን አስሮ ወሰደ፤
“ስለዚህ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምላችሁ ይህ ነው፦ ‘በሰታቴው ውስጥ ያለው ሥጋ እናንተ የገደላችኋቸው ሰዎች ናቸው፤ ይህችም ከተማ ሰታቴዋ ነች፤ እናንተ ግን ከከተማይቱ ትወገዳላችሁ።
“ሔልዳይ፥ ጦቢያና ይዳዕያ የተባሉት ስደተኞች የሰጡትን ብርና ወርቅ ይዘህ ሳትዘገይ አሁኑኑ ወደ ሶፎንያስ ልጅ ወደ ኢዮስያስ ቤት ሂድ፤ እነዚህ ሁሉ ሰዎች ከባቢሎን የተመለሱ ምርኮኞች ናቸው፤