ይህንንም የማደርገው ሰሎሞን እኔን ትቶ ባዕዳን የሆኑትን ዐስታሮት ተብላ የምትጠራውን የሲዶና አምላክ፥ ከሞሽ ተብሎ የሚጠራውን የሞአብ አምላክና ሚልኮም ተብሎ የሚጠራውን የዐሞን አምላክ ስላመለከ ነው፤ ሰሎሞን ለእኔ ታዛዥ አልሆነም፤ እርሱ አባቱ ዳዊት ለእኔ ይታዘዝ እንደ ነበር ሕጎቼንና ትእዛዞቼን ባለመጠበቁ በድሎአል።
2 ነገሥት 23:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ከርኲሰት ተራራ በስተ ደቡብ ዐስታሮት ተብላ ለምትጠራው ለሲዶና አምላክ፥ ከሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞአብ አምላክና ሞሌክ ተብሎ ለሚጠራው ለዐሞን አምላክ ንጉሥ ሰሎሞን አሠርቶአቸው የነበሩት አጸያፊዎች ምስሎች ሁሉ የረከሱ መሆናቸውን አስገነዘበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ ከርኩሰት ኰረብታ በስተ ደቡብ የነበሩትን የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለሲዶናውያን የርኩሰት አምላክ ለአስታሮት፣ ለሞዓብ ሕዝቦች የርኩሰት አምላክ ለካሞሽ፣ ለአሞን ሕዝቦች የርኩሰት አምላክ ለሚልኮም ያሠራቸውን የኰረብታ ላይ ማምለኪያዎች ንጉሡ አረከሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ከርኲሰት ተራራ በስተ ደቡብ ዐስታሮት ተብላ ለምትጠራው ለሲዶና አምላክ፥ ከሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞዓብ አምላክና ሞሌክ ተብሎ ለሚጠራው ለዐሞን አምላክ ንጉሥ ሰሎሞን አሠርቶአቸው የነበሩት አጸያፊዎች ምስሎች ሁሉ የረከሱ መሆናቸውን አስገነዘበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢየሩሳሌምም ፊት ለፊት በርኵስት ተራራ ቀኝ የነበሩትን፥ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለሲዶናውያን ርኵስት ለአስታሮት፥ ለሞዓብም ርኵሰት ለካሞሽ፥ ለአሞንም ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ ያሠራቸውን መስገጃዎች ንጉሡ ርኩስ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኢየሩሳሌም ፊት ለፊት በርኵሰት ተራራ ቀኝ የነበሩትን፥ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለሲዶናውያን ርኵሰት ለአስታሮት ለሞዓብም ርኵሰት ለካሞሽ ለአሞንም ልጆች ርኵሰት ለሚልኮም ያሠራቸውን መስገጃዎች ንጉሡ ርኩስ አደረገ። |
ይህንንም የማደርገው ሰሎሞን እኔን ትቶ ባዕዳን የሆኑትን ዐስታሮት ተብላ የምትጠራውን የሲዶና አምላክ፥ ከሞሽ ተብሎ የሚጠራውን የሞአብ አምላክና ሚልኮም ተብሎ የሚጠራውን የዐሞን አምላክ ስላመለከ ነው፤ ሰሎሞን ለእኔ ታዛዥ አልሆነም፤ እርሱ አባቱ ዳዊት ለእኔ ይታዘዝ እንደ ነበር ሕጎቼንና ትእዛዞቼን ባለመጠበቁ በድሎአል።
ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ተራራ ላይ አጸያፊዎች ለሆኑት ከሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞአባውያን አምላክና ሞሎክ ተብሎ ለሚጠራው ለዐሞናውያን አምላክ የመስገጃ ስፍራዎችን አዘጋጀላቸው።
እንዲህም አልኳቸው፦ “የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ኃጢአት የሠራው በእንደዚህ ያለ ጋብቻ አይደለምን? ከብዙ ሕዝቦች መካከል እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ አልነበረም። እግዚአብሔርም ወዶት በሕዝቡ በእስራኤል ላይ አነገሠው፤ እርሱ ግን በባዕዳን ሴቶች አማካይነት ኃጢአት ሠራ። በዚህ ዐይነቱ ኃጢአት ላይ ወደቀ፤
“የዚህን እንጨት ግማሹን አነደድኩት፤ በፍሙም ዳቦ ጋገርኩበት፤ ሥጋም ጠብሼበት በላሁ፤ አሁን እንግዲህ ቀሪውን ቊራጭ እንጨት ለጣዖት ላውለውን? በአንድ ቊራጭ እንጨት ፊት ወድቄ ልስገድን?” ብሎ የሚያስብ ዕውቀት ወይም ማስተዋል ያለው አንድም ሰው የለም።
የይሁዳ ሕዝብ ሆይ፥ በከተሞቻችሁ ልክ ብዙ አማልክት አሉአችሁ፤ በኢየሩሳሌምም መንገዶች ልክ አጸያፊ ለሆነው በዓል ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ መሥዋዕት የምታቀርቡበት ብዙ መሠዊያዎችን ሠርታችኋል።
“የሞአብ ሕዝብ ሆይ! በኀይላችሁና በሀብታችሁ ብዛት ተማምናችሁ ነበር፤ አሁን ግን እነሆ እናንተ ራሳችሁ እንኳ ትማረካላችሁ፤ ከሞሽ ተብሎ የሚጠራው ጣዖት ከልዑላን መሳፍንትና ከካህናቱ ጋር ተማርኮ ይወሰዳል።
ጣራ ላይ ወጥተው ለፀሐይ፥ ለጨረቃና ለከዋክብት የሚሰግዱትን አጠፋለሁ፤ እኔን እያመለኩና በስሜ እየማሉ፥ ዘወር ብለው ደግሞ ሚልኮም ተብሎ በሚጠራው ጣዖት ስም የሚምሉትን እደመስሳለሁ።
ሞአብ ሆይ! ወዮልሽ! እናንተ የከሞሽ ሰዎች ሆይ! ትደመሰሳላችሁ፤ ወንዶች ልጆቹን ስደተኞች እንዲሆኑ አደረጋቸው፤ ሴቶች ልጆቹንም ንጉሥ ሲሖን እንዲማረኩ አደረገ።
እስራኤላውያን ባዓልና ዐስታሮት የተባሉትን ባዕዳን አማልክት እንዲሁም የሶርያን፥ የሲዶናን፥ የሞአብን፥ የዐሞንንና የፍልስጥኤምን አማልክት በማምለክ እንደገና እግዚአብሔርን በደሉ፤ እርሱንም ማምለክ ተዉ፤
ከዚያም በኋላ እነርሱ ‘አንተን ትተን በዓልንና ዐስታሮትን በማምለካችን በድለናል፤ አሁንም ከጠላቶቻችን አድነን፤ እናመልክህማለን!’ ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።