1 ተሰሎንቄ 3:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም በደረሰባችሁ መከራ እንዳትናወጡ ያደርጋችኋል፤ ይህ መከራ ለእኛ የተወሰነልን ዕጣ መሆኑን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም በዚህ ፈተና ማንም እንዳይናወጥ ነው። እኛም ለዚህ ነገር እንደ ተመደብን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ መከራ ማንም እንዳይናወጥ፥ ለዚህ እንደ ተሾምን ራሳችሁ ታውቃላችሁና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህ መከራ ማንም እንዳይናወጥ፥ ለዚህ እንደ ተመረጥን ራሳችሁ ታውቃላችሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚህ መከራ ማንም እንዳይናውጥ፥ ለዚህ እንደ ተመረጥን ራሳችሁ ታውቃላችሁና። |
ነገር ግን ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ሰዎች እናንተን ይይዙአችኋል፤ ያሳድዱአችኋል፤ ወደ ምኲራብና ወደ ወህኒ ቤትም አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ስለ ስሜም ወደ ነገሥታትና ወደ ገዥዎች ይወስዱአችኋል።
ይህን ለእናንተ መናገሬ በእኔ ሆናችሁ ሰላም እንዲኖራችሁ ብዬ ነው፤ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፥ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”
በእነዚያም አገሮች ሁሉ አማኞች በእምነታቸው እንዲጸኑ በማበረታታትና በመምከር “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ብዙ መከራ መቀበል አለብን” እያሉ አስተማሩአቸው።
ይህ ነቢይ ወደ እኛ ቀረበ፤ የጳውሎስን መታጠቂያ ወስዶ የገዛ እጆቹንና እግሮቹን አሰረና “መንፈስ ቅዱስ የዚህን መታጠቂያ ባለቤት በኢየሩሳሌም ያሉ አይሁድ እንደዚህ አስረው ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል ይላል” አለ።
ጳውሎስ ግን “እንደዚህ እያለቀሳችሁ ስለምን ልቤን በሐዘን ትሰብሩታላችሁ? እኔ ስለ ጌታ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመታሰር ብቻ ሳይሆን ለመሞትም ዝግጁ ነኝ” ሲል መለሰ።
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ፤ ለጌታ ሥራ የምትደክሙት በከንቱ አለመሆኑን ዐውቃችሁ፥ ሳታቋርጡ ዘወትር የጌታን ሥራ ለመሥራት ትጉ።
እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት ተፈርዶባቸው ወደሚገደሉበት ቦታ ከሚወሰዱት ሰዎች መካከል የመጨረሻዎቹ ያደረገን ይመስለኛል፤ ከዚህም የተነሣ በዓለም ሁሉ በመላእክትም ሆነ በሰዎች ፊት እንደ ትርኢት ሆነን እንታያለን፤
ተቃዋሚዎቻችሁንም በምንም ነገር አትፍሩአቸው፤ ይህም ድፍረታችሁ ለእነርሱ የመጥፋታቸው ምልክት ሲሆን ለእናንተ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ የመዳኛችሁ ምልክት ነው።
ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት ጸንታችሁ ስትኖሩ ብቻ ነው፤ ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና በዓለም ላይ ላሉት ሰዎች ሁሉ የተሰበከ ነው፤ እኔ ጳውሎስም አገልጋይ የሆንኩት ለዚሁ ወንጌል ነው።
ስለዚህም ምንም እንኳ ብዙ ችግርና ሥቃይ ቢደርስባችሁ እናንተ እንዴት ታጋሾችና በእምነታችሁ የጸናችሁ መሆናችሁን በመናገር እኛ በሌሎች አብያተ ክርስቲያን መካከል ሆነን በእናንተ እንመካለን።
እንግዲህ ስለ ጌታችን ለመመስከር አትፈር፤ ስለ እርሱ በታሰርኩት በእኔም አትፈር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በሚሰጥህ ኀይል ስለ ወንጌል ከእኔ ጋር መከራን ተቀበል።
ወደ ፊት የሚደርስብህን መከራ አትፍራ፤ እነሆ፥ እንድትፈተኑ ከእናንተ አንዳንዶቹን ዲያብሎስ ወደ እስር ቤት ያገባችኋል፤ ዐሥር ቀንም መከራ ትቀበላላችሁ፤ እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ የሕይወት አክሊል እሰጥሃለሁ።
አንተ የሰይጣን ዙፋን ባለበት ስፍራ መኖርህን ዐውቃለሁ፤ ይሁን እንጂ ስሜን አጥብቀህ ይዘሃል፤ በእኔ ላይ ያለህን እምነት አልካድክም፤ ታማኝ ምስክሬ የነበረው አንቲጳስ ሰይጣን በሚኖርበት በእናንተ ከተማ በተገደለ ጊዜ እንኳ በእኔ ማመንህን አልተውክም።