እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ዐመፀኞችና እምቢተኞች አይሆኑም፤ እነዚያ እግዚአብሔርን በማመን የጸኑ አልነበሩም፤ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው አልኖሩም።
1 ሳሙኤል 8:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እነርሱን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ፊታቸውን መልሰው ከእኔ በመራቅ ባዕዳን አማልክትን ሲያመልኩ ኖረዋል፤ እንግዲህ በእኔ ላይ ሲያደርጉት የነበረውን ሁሉ እነሆ በአንተም ላይ መፈጸም ጀምረዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ዕለት አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ትተው ሌሎች አማልክትን በማምለክ ያደረጉትን ሁሉ በአንተም ላይ እያደረጉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ቀን አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ትተው ሌሎች አማልክትን በማምለክ ያደረጉትን ሁሉ በአንተም ላይ እያደረጉ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግብፅ ካወጣኋቸው ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ትተው እንግዶች አማልክትን በማምለካቸው እንደ ሠሩት ሥራ ሁሉ እንዲሁ በአንተ ደግሞ ያደርጉብሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግብጽ ካወጣኋቸው ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ትተው እንግዶች አማልክት በማምለካቸው እንደ ሠሩት ሥራ ሁሉ እንዲሁ በአንተ ደግሞ ያደርጉብሃል። |
እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ዐመፀኞችና እምቢተኞች አይሆኑም፤ እነዚያ እግዚአብሔርን በማመን የጸኑ አልነበሩም፤ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው አልኖሩም።
“ምነው በግብጽ ሳለን እግዚአብሔር በገደለን ኖሮ፥ በዚያ ሌላው ቢቀር ሥጋም ሆነ ሌላ ምግብ የፈለግነውን ያኽል መመገብ እንችል ነበረ፤ እናንተ ግን ሁላችንም በራብ እንድናልቅ ወደዚህ በረሓ አወጣችሁን።”
ስለዚህም “የምንጠጣው ውሃ ስጠን” ብለው በሙሴ ላይ አጒረመረሙ። ሙሴም “ስለምን ትወቅሱኛላችሁ? ስለምንስ እግዚአብሔርን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው።
ሕዝቡ ሙሴ ከተራራው ሳይወርድ እዚያ ብዙ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ በአንድነት በመሰብሰብ አሮንን ከበው “ያ ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣን ሙሴ ምን እንደ ደረሰበት አናውቅም፤ ስለዚህ በፊት በፊታችን እየሄዱ የሚመሩን አማልክትን ሥራልን” አሉት።
በዚያም ቃል ኪዳን መሠረት፥ ዕብራውያን ባሪያዎች ያሉአቸው ሁሉ ስድስት ዓመት ካገለገሉአቸው በኋላ በሰባተኛው ዓመት ነጻ እንዲያወጡአቸው አዘዝኩ፤ ነገር ግን የቀድሞ አባቶቻችሁ ሊታዘዙኝም ሆነ ቃሌን ሊሰሙ አልፈለጉም፤
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! በእኔ ላይ ወደ ዐመፁት ወደ እስራኤል ሕዝብ እልክሃለሁ፤ እነርሱና የቀድሞ አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ በእኔ ላይ እንዳመፁ ናቸው።
ስለዚህ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ እጅግ ተቈጥቶ እንዲህ አለ፦ “ይህ ሕዝብ ከአባቶቹ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አፈረሰ፤ ትእዛዜን አልጠበቀም።
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፦ “ሕዝቡ የሚሉህን ነገር ሁሉ ተቀበል፤ እነርሱ የናቁት አንተን አይደለም፤ በእነርሱ ላይ ነግሼ እንዳልኖር፥ እነርሱ የናቁት እኔን ነው።
ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ የሚሉህን ተቀበል፤ ነገር ግን ንጉሦቻቸው ወደ ፊት በእነርሱ ላይ የሚፈጽሙባቸውን ነገር ሁሉ በመግለጥ በብርቱ አስጠንቅቃቸው።”