Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 6:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን እንደገና በደሉ፤ እግዚአብሔርም ለምድያማውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ሰባት ዓመት ሙሉ ገዙአቸው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እንደ ገና እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ እግዚአብሔርም ለምድያማውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ሰባት ዓመት ገዟቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እንደገና እስራኤላውያን በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ጌታም ለምድያማውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ሰባት ዓመት ገዟቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድ​ያም እጅ ሰባት ዓመት አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፥ እግዚአብሔርም በምድያም እጅ ሰባት ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 6:1
16 Referencias Cruzadas  

እርስዋም ዚምራንን፥ ዮቅሻንን፥ መዳንን፥ ምድያምን፥ ዩሽባቅንና ሹሐን ወለደችለት።


የምድያም ነጋዴዎች የሆኑ እስማኤላውያን በዚያ በኩል ያልፉ ነበር፤ ስለዚህ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጒድጓድ ጐትተው በማውጣት ለእነዚህ እስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ወደ ግብጽ ይዘውት ሄዱ።


የኢትዮጵያ ሰፈር ሲጨነቅ፥ የምድያምም ሰዎች ሲንቀጠቀጡ አየሁ።


ሞአባውያን ለምድያማውያን ሽማግሌዎች “ይህ የምታዩት የሕዝብ ብዛት በሬ በመስክ የሚገኘውን ሣር ሁሉ ጠራርጎ እንደሚበላ በዙሪያችን ያለውን ነገር ሁሉ ጠራርጎ የሚያጠፋ ነው” አሉአቸው። ስለዚህ በዚያን ጊዜ የሞአብ ንጉሥ የነበረው የጺጶር ልጅ ባላቅ፥


እንግዲህ ሌላ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎን፥ ስለ ባራቅ፥ ስለ ሶምሶን፥ ስለ ዮፍታሔ፥ ስለ ዳዊት፥ ስለ ሳሙኤል፥ ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥረኛል፤


ስለዚህ እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ላይ ተቈጣ፤ ለፍልስጥኤማውያንና ለዐሞናውያን አሳልፎ ሰጣቸው።


ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ክፉ ሥራ በመሥራት እግዚአብሔርን በደሉ። በዓሊም ተብለው የሚጠሩትን ባዕዳን አማልክት አመለኩ፤


ጌዴዎንም እንዲህ አለው፦ “ጌታዬ ሆይ! ታዲያ፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ሁሉ ችግር እንዴት ሊደርስብን ቻለ? አባቶቻችን እንደ ነገሩን እግዚአብሔር ያደርገው የነበረ ድንቅ ሥራ ሁሉ ዛሬ የት አለ? ከግብጽ እንዴት እንዳወጣቸውም ነግረውን ነበር፤ ዛሬ ግን እግዚአብሔር እኛን በመተው እንደ ፈለጉ ያደርጉን ዘንድ ለምድያማውያን አሳልፎ ሰጥቶናል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos