የይሁዳ ሰዎች ግን ለእግዚአብሔር ቃል ታዛዦች ሆነው አልተገኙም፤ ይልቁንም ምናሴ እስራኤላውያን ወደፊት እየገፉ ሲመጡ እግዚአብሔር ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋላቸው ሕዝቦች ይፈጽሙት ከነበረው ይበልጥ ወደ ከፋ ኃጢአት መራቸው።
1 ሳሙኤል 8:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ ሕዝቡ ሳሙኤል ለነገራቸው ቃል ሁሉ ዋጋ አልሰጡትም፤ ይልቁንም “እንደዚህ አይደለም! እኛ ንጉሥ እንዲኖረን እንፈልጋለን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡ ግን ሳሙኤልን መስማት እንቢ በማለት፤ እንዲህ አሉ፤ “አይሆንም፤ ንጉሥ እንዲነግሥልን እንፈልጋለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡ ግን ሳሙኤልን መስማት እምቢ በማለት፥ እንዲህ አሉ፦ “አይሆንም፤ ንጉሥ እንዲነግሥልን እንፈልጋለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡ ግን የሳሙኤልን ነገር ይሰሙ ዘንድ እንቢ አሉ፥ “እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አንግሥልን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡ ግን የሳሙኤልን ነገር ይሰማ ዘንድ እንቢ አለ፦ እንዲህ አይሁን፥ ነገር ግን ንጉሥ ይሁንልን፥ |
የይሁዳ ሰዎች ግን ለእግዚአብሔር ቃል ታዛዦች ሆነው አልተገኙም፤ ይልቁንም ምናሴ እስራኤላውያን ወደፊት እየገፉ ሲመጡ እግዚአብሔር ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋላቸው ሕዝቦች ይፈጽሙት ከነበረው ይበልጥ ወደ ከፋ ኃጢአት መራቸው።
ስጠራ ማንም ስላልመለሰልኝ፥ ስናገር ማንም ስላላዳመጠኝ ነገር በፊቴ ክፉ የሆነውን ነገር ስላደረጉና የማያስደስተኝን ስለ መረጡ እኔም በእነርሱ ላይ ቅጣት አመጣባቸዋለሁ።”
ስለዚህም ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሕዝቤ አንተ ምን እንደምትናገር ለማዳመጥ ብቻ ይሰበሰባሉ፤ ነገር ግን የምትነግራቸውን ሁሉ አይፈጽሙም፤ የምትናገረውን ቃል የሚወዱት መስለው ይታያሉ፤ ነገር ግን ከበዝባዥነታቸው አይመለሱም፤
እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ንጉሣችሁ ሆኖ ሳለ የአሞን ንጉሥ ናዖስ በእናንተ ላይ መነሣቱን ባያችሁ ጊዜ ‘አይሆንም ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁ።