1 ሳሙኤል 28:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም ሳኦልን “ዕረፍት የምትነሣኝ ስለምንድን ነው? ስለምንስ ከመቃብር እንድነሣ አስጠራኸኝ?” አለው። ሳኦልም “እነሆ፥ እኔ በታላቅ ችግር ላይ ነኝ! ፍልስጥኤማውያን ከእኔ ጋር ጦርነት በማድረግ ላይ ናቸው፤ እግዚአብሔርም እኔን ትቶኛል፤ በነቢይም ሆነ በሕልም መልስ ሊሰጠኝ አልፈለገም፤ ስለዚህም ምን ማድረግ እንደሚገባኝ ትነግረኝ ዘንድ እንድትነሣ አስጠራሁህ” ሲል መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም ሳኦልን፣ “አስነሥተህ የምታውከኝ ለምንድን ነው?” አለው። ሳኦልም፣ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ፍልስጥኤማውያን እየወጉኝ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእኔ ርቋል፤ በነቢያትም ሆነ በሕልም አልመለሰልኝም፤ ስለዚህ ምን ማድረግ እንደሚገባኝ እንድትነግረኝ ጠራሁህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “አስነሥተህ የምታውከኝ ለምንድነው?” አለው፤ ሳኦልም፥ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ፍልስጥኤማውያን እየወጉኝ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእኔ ርቋል፤ በነቢያትም ሆነ በሕልም አልመለሰልኝም፤ ስለዚህ ምን ማድረግ እንደሚገባኝ እንድትነግረኝ ጠራሁህ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “ለምን አወክኸኝ? ለምንስ አስነሣኸኝ?” አለው። ሳኦልም መልሶ፥ “ፍልስጥኤማውያን ይወጉኛልና እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ እግዚአብሔርም ከእኔ ርቆአል፤ በነቢያት ወይም በሕልም አላሚዎች አልመለሰልኝም፤ ስለዚህም የማደርገውን ታስታውቀኝ ዘንድ ጠራሁህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ሳኦልን፦ ለምን አወክኽኝ? ለምንስ አስነሣኸኝ? አለው። ሳኦልም መልሶ፦ ፍልስጥኤማውያን ይወጉኛልና እጅግ ተጨንቄአለሁ፥ እግዚአብሔርም ከእኔ ርቆአል፥ በነቢያት ወይም በሕልም አልመለሰልኝም፥ ስለዚህም የማደርገውን ታስታውቀኝ ዘንድ ጠራሁህ አለው። |
ከዚህ በኋላ በግራው በኩል ያሉትንም እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለተከታዮቹ መላእክት ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ!
ከዚያም በኋላ “ሶምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” አለችው፤ እርሱም ከእንቅልፉ ነቅቶ “እንደ ወትሮው በጣጥሼ እሄዳለሁ” ብሎ አሰበ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተለየው አላወቀም ነበር፤
ስለዚህም ዳዊት “ሄጄ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ልጣልባቸውን?” ሲል የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አዎ! በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ በመጣል ቀዒላን ከጥፋት አድን” ሲል መለሰለት።
ከዚህም የተነሣ ዳዊት እንደገና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም “እኔ በፍልስጥኤማውያን ላይ ድልን ስለማቀዳጅህ ሄደህ በቀዒላ ላይ አደጋ ጣል” አለው።
ስለዚህም ምን ማድረግ እንደሚገባው እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔር ግን በሕልም ወይም በኡሪም ወይም በነቢያት አማካይነት መልስ እንዲሰጠው አልፈቀደም።
ሳኦልም ልብሱን ለውጦ ማንነቱ እንዳይታወቅ በማድረግ በሌሊት ሁለት ሰዎች አስከትሎ ሴትዮዋን ለማየት ሄደ፤ እዚያም እንደ ደረሰ “መናፍስትን ጠይቀሽ ወደ ፊት ስለሚሆነው ነገር አስረጂኝ፤ ስሙንም የምጠራልሽን ሰው አስነሽልኝ” አላት።
ሰዎቹ ሁሉ በሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው መማረክ ምክንያት ተማርረው ስለ ነበረ በድንጋይ ሊወግሩት በመነጋገራቸው ዳዊት በታላቅ አደጋ ላይ ነበር። እርሱ ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አጽናና፤