የቤቱም አዛዥ “በዚህ ጉዳይ ጭንቀትና ፍርሀት አይድረስባችሁ፤ የእናንተና የአባታችሁ አምላክ ይህን ገንዘብ በየስልቻዎቻችሁ አስቀምጦላችሁ ይሆናል፤ የእናንተን ገንዘብ ግን እኔ ተቀብዬአለሁ” አላቸው። ከዚህ በኋላ ስምዖንን ወደ እነርሱ አመጣው።
1 ሳሙኤል 25:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለናባልም ይነግሩት ዘንድ እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጣቸው፦ “ሰላም ላንተ፥ ሰላም ለቤትህ፥ ሰላም ያንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን ብላችሁ ሰላምታ አቅርቡለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም በሉት፤ ‘ዕድሜህ ይርዘም! ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ሰላም ለቤተ ሰብህና የአንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም በሉት፤ ‘ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ሰላም ለቤተሰብህና የአንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም በሉት፥ “ደኅንነትና ሰላም ለአንተና ለቤትህ፥ ለአንተም ለሆኑት ሁሉ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደኅንነት ኑር፥ ለአንተና ለቤትህም ለአንተም ላሉት ሁሉ ሰላም ይሁን። |
የቤቱም አዛዥ “በዚህ ጉዳይ ጭንቀትና ፍርሀት አይድረስባችሁ፤ የእናንተና የአባታችሁ አምላክ ይህን ገንዘብ በየስልቻዎቻችሁ አስቀምጦላችሁ ይሆናል፤ የእናንተን ገንዘብ ግን እኔ ተቀብዬአለሁ” አላቸው። ከዚህ በኋላ ስምዖንን ወደ እነርሱ አመጣው።
አሒማዓጽም ድምፁን ከፍ አድርጎ ለንጉሡ ሰላምታ ሰጠ፤ በንጉሡም ፊት በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ “ንጉሥ ሆይ! በአንተ ላይ በዐመፅ የተነሣሡትን ድል እንድታደርግ ስለ ረዳህ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!” አለ።
የእግዚአብሔር መንፈስ የሠላሳዎቹ መሪ በሆነው በዐማሳይ ላይ ወረደ፤ እርሱም፦ “ዳዊት ሆይ! እኛ የአንተ ነን! የእሴይ ልጅ ዳዊት ሆይ! እኛ ከአንተ ጋር ነን! ለአንተና አንተን ለሚረዱ ሁሉ ሰላም ይሁን! እግዚአብሔር ከአንተ ጋር በመሆን ይረዳሃል፤” በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ፤ ዳዊትም እነርሱን በደስታ ተቀብሎ በሠራዊቱ ውስጥ አለቆች አደረጋቸው።
“ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ዐይነት አይደለም፤ ልባችሁ አይጨነቅ፤ ደግሞም አይፍራ።