Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 25:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 በጎችህንም እንደምታሸልት ሰምቶአል፤ እረኞችህ ከእኛ ጋር በነበሩበት ጊዜም ሁሉ ምንም ዐይነት ጒዳት እንዳላደረስንባቸው እንድታውቅ ይፈልጋል፤ በቀርሜሎስ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ ከመንጋቸው አንድ እንኳ አልተወሰደባቸውም፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ ‘በዚህ ጊዜ በጎች እንደምትሸልት ሰምቻለሁ፤ እረኞችህ ከእኛ ጋራ በነበሩበት ጊዜ፣ ያደረስንባቸው ጕዳት የለም፤ ቀርሜሎስ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ፣ የጠፋባቸው አንዳች ነገር አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በዚህ ጊዜ በጎች እንደምትሸልት ሰምቻለሁ፤ እረኞችህ ከእኛ ጋር በነበሩበት ጊዜ፥ ያደረስንባቸው ጉዳት የለም፤ ቀርሜሎስ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ፥ የጠፋባቸው አንዳች ነገር አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አሁ​ንም በጎ​ችህ እን​ደ​ሚ​ሸ​ለቱ ከእኛ ጋር በም​ድረ በዳ ያሉ ሰዎች ነገ​ሩን፤ እኛም አል​ከ​ለ​ከ​ል​ና​ቸ​ውም፤ በቀ​ር​ሜ​ሎ​ስም በነ​በ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ ከመ​ን​ጋ​ቸው ይሰ​ጡን ዘንድ አላ​ዘ​ዝ​ና​ቸ​ውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አሁንም በጎችህን እንድትሸልት ሰምቻለሁ፥ እረኞችህም ከእኛ ጋር ነበሩ፥ ከቶ አልበደልናቸውም፥ በቀርሜሎስም በተቀመጡበት ዘመን ሁሉ ከመንጋው አንዳች አልጎደለባቸውም።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 25:7
9 Referencias Cruzadas  

ከሁለት ዓመት በኋላ አቤሴሎም በኤፍሬም ከተማ አጠገብ በዓለ ሐጾር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በጎቹን ይሸልት ነበር፤ ስለዚህም የንጉሡን ወንዶች ልጆች ሁሉ ለግብዣ ወደዚያ ጠራ።


ወደ ንጉሥ ዳዊትም ሄዶ “ንጉሥ ሆይ! በጎቼን እየሸለትሁ ነው፤ ስለዚህ አንተና መኳንንትህ መጥታችሁ የግብዣው ተካፋዮች እንድትሆኑልኝ ትፈቅዳለህን?” አለው።


ወታደሮችም መጥተው፥ “እኛስ ምን እናድርግ?” አሉት፤ እርሱም፦ “የሰው ገንዘብ በግፍ ነጥቃችሁ አትውሰዱ፤ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፤ የራሳችሁ ደመወዝ ይብቃችሁ፤” አላቸው።


ይህም ከሆነ በዚህ በጠማማና በመጥፎ ትውልድ መካከል ነውርና ነቀፋ የሌለባችሁ ንጹሓን የእግዚአብሔር ልጆች በመሆን በዚህ ዓለም እንደ ከዋክብት ታበራላችሁ።


አእምሮአችሁ በእነዚህ ከሁሉ በሚበልጡና በሚያስመሰግኑ መልካም ነገሮች የተመላ ይሁን፤ በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! እውነተኛ፥ ክቡር፥ ትክክለኛ፥ ንጹሕ፥ አስደሳችና ምስጉን የሆኑ ነገሮችን ሁሉ አስቡ።


የተጨነቁ፥ ዕዳ ያለባቸው፥ እንዲሁም ሆድ የባሳቸው አንዳንድ ሰዎች ወደ እርሱ ስለ ሄዱ ብዛታቸው በድምሩ እስከ አራት መቶ ደረሰ፤ ዳዊትም የእነርሱ መሪ ሆነ።


ዳዊትም በልቡ እንዲህ እያለ ያስብ ነበር፤ “የዚያን የማይረባ ሰው ሀብት በዚህ በረሓ ለምን ስጠብቅ ቈየሁ? የእርሱ ከሆነው ንብረት ምንም ነገር ተሰርቆበት አያውቅም፤ ታዲያ እኔ ስላደረግሁለት መልካም ነገር እርሱ የሚከፍለኝ ወሮታ ይህ ሆኖ ቀረ!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos