እንግዲህ የጌታዬን ዐደራ በእውነት ተቀብላችሁ እርሱን ደስ ለማሰኘት የምትፈቅዱ እንደ ሆነ ንገሩኝ፤ የማትፈቅዱም እንደ ሆነ ቊርጡን ንገሩኝ፤ እኔም እግዚአብሔር ወደሚመራኝ እሄዳለሁ።”
1 ሳሙኤል 20:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስለ ተማመንን የሰጠኸኝን የተቀደሰ ተስፋ በመጠበቅ እባክህ ለእኔ ለአገልጋይህ መልካም ነገር አድርግልኝ፤ ወንጀለኛ ሆኜ ከተገኘሁ ግን አንተው ራስህ ግደለኝ እንጂ እንዲገድለኝ ወደ አባትህ ለምን ትወስደኛለህ?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ግን፤ ለአገልጋይህ በጎነትን አሳይ፣ ከአገልጋይህ ጋራ በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን ገብታችኋልና። እኔ በደለኛ ከሆንሁ፣ አንተው ራስህ ግደለኝ፤ ለምንስ ለአባትህ አሳልፈህ ትሰጠኛለህ!” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ግን ከአገልጋይህ ጋር በጌታ ፊት ቃል ኪዳን ገብታችኋልና ለአገልጋይህ በጎነትን አሳይ። እኔ በደለኛ ከሆንኩ፥ አንተው ራስህ ግደለኝ፤ ለምንስ ለአባትህ አሳልፈህ ትሰጠኛለህ!” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ከባሪያህ ጋር አድርገሃልና ለባሪያህ ቸርነትን አድርግ፤ በደል ግን ቢገኝብኝ አንተ ግደለኝ፤ ለምን ወደ አባትህ ታደርሰኛለህ?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ከባሪያህ ጋር አድርገሃልና ለባሪያህ ቸርነት አድርግ፥ በደል ግን ቢገኝብኝ አንተ ግደለኝ፥ ለምን ወደ አባትህ ታደርሰኛለህ? |
እንግዲህ የጌታዬን ዐደራ በእውነት ተቀብላችሁ እርሱን ደስ ለማሰኘት የምትፈቅዱ እንደ ሆነ ንገሩኝ፤ የማትፈቅዱም እንደ ሆነ ቊርጡን ንገሩኝ፤ እኔም እግዚአብሔር ወደሚመራኝ እሄዳለሁ።”
ያዕቆብ የሚሞትበት ቀን በተቃረበ ጊዜ ልጁን ዮሴፍን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “በፊትህ ሞገስን አግኝቼ ከሆነ፥ በምሞትበት ጊዜ በግብጽ ምድር እንዳትቀብረኝ፥ እጅህን በጒልበቴ ላይ አኑረህ በመሐላ ቃል ግባልኝ።
አቤሴሎምም “አንተ እኔ ስጠራህ ስላልመጣህ ነው፤ ወደ ንጉሡ ሄደህ ‘ከገሹር ወጥቼ ወደዚህ ለምን መጣሁ? እዚያው ቈይቼ ብሆን ኖሮ በተሻለኝ ነበር’ ብለህ ስለ እኔ ሁኔታ ጠይቅልኝ፤ እንዲሁም ከንጉሡ ጋር መገናኘት እችል ዘንድ ሁኔታዎችን አመቻችልኝ፤ እኔ በደለኛ ሆኜ ከተገኘሁ ሞት ይፍረድብኝ” አለው።
ዳዊትም ወደ እነርሱ ቀርቦ እንዲህ አላቸው፤ “ወደዚህ የመጣችሁት በወዳጅነት ልትረዱኝ ከሆነ መልካም ነው፤ በደስታ እቀበላችኋለሁ፤ ከእኛም ጋር ሁኑ! እኔ ምንም ሳላደርጋችሁ ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ ከሆነ ግን የቀድሞ አባቶቻችን አምላክ ተመልክቶ ይፍረደው።”
በደለኛ ከሆንኩ ወይም በሞት የሚያስቀጣ በደል ካደረግሁ ከሞት ልዳን አልልም፤ ነገር ግን የእነርሱ ክስ ከንቱ ከሆነ ማንም ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጠኝ አይችልም፤ እኔ ወደ ሮማ ንጉሠ ነገሥት ይግባኝ ብዬአለሁ።”
ሰዎቹም እንዲህ አሉአት፤ “እኛ በገባንልሽ ቃል መሠረት ባንፈጽም እግዚአብሔር በሞት ይቅጣን! እኛ ያደረግነውን ሁሉ ለማንም ባትነግሪ፥ እግዚአብሔር ይህቺን ምድር ለእኛ አሳልፎ በሚሰጠን ጊዜ ለአንቺ መልካም ነገር ለማድረግ ቃል እንገባለን።”
“ከሁሉ የሚበልጥ ኀያል እግዚአብሔር ነው! እርሱ የሁሉ ጌታ ነው! እርሱ ከሁሉ የሚበልጥ ኀያል አምላክ ነው! እኛ ስለምን ይህን እንደ ሠራን እርሱ ያውቃል፤ እናንተም ስለምን እንደ ሠራነው እንድታውቁት እንፈልጋለን፤ በእውነት ካመፅንና በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት አጓድለን ከተገኘን፥ በሕይወት እንድንኖር አትፍቀዱልን፤
ናዖሚ ምራቶችዋን እንዲህ አለቻቸው፤ “እንግዲህ ወደየቤታችሁ ተመለሱና ከእናቶቻችሁ ጋር ኑሩ፤ ለእኔና ለሟቾቹ ባሎቻችሁ መልካም ነገር እንዳደረጋችሁ፥ እንዲሁም እግዚአብሔር ለእናንተ መልካም ነገር ያድርግላችሁ፤
ሳኦልና ዳዊት ንግግራቸውን ከጨረሱ በኋላ የሳኦል ልጅ ዮናታን ከዳዊት ጋር እጅግ የተቀራረበ አንድነት መሠረተ፤ እንደ ራሱም አድርጎ ወደደው፤
ስለዚህ ሁለቱም እርስ በርሳቸው የወዳጅነት ቃል ኪዳን አደረጉ፤ ከዚህም በኋላ ዳዊት በሖሬሽ መኖሩን ቀጠለ፤ ዮናታንም ወደ ቤቱ ተመልሶ ሄደ።