ከዚህም በኋላ ከተከታዮቹ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሶ መጥቶ፦ “ከእስራኤል አምላክ በቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እነሆ፥ አሁን ተረዳሁ፤ ስለዚህም ጌታዬ ሆይ፥ እባክህ ይህን ስጦታ ተቀበለኝ” አለው።
1 ሳሙኤል 17:47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚህ የተሰበሰቡት ሁሉ እግዚአብሔር የሚያድነው በሰይፍና በጦር አለመሆኑን ያውቃሉ፤ ጦርነቱ የእግዚአብሔር ነውና፤ በእናንተም ላይ ድልን እንድንጐናጸፍ ያደርገናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እዚህ የተሰበሰቡትም ሁሉ፣ እግዚአብሔር የሚያድነው በሰይፍ ወይም በጦር እንዳልሆነ ያውቃሉ፤ ሰልፉ የእግዚአብሔር ስለ ሆነም ሁላችሁን በእጃችን አሳልፎ ይሰጣል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እዚህ የተሰበሰቡትም ሁሉ ጌታ ያለ ሰይፍ ወይም ያለ ጦር እንደሚያድን ያውቃሉ፤ ሰልፉ የጌታ ስለ ሆነም ሁላችሁን በእጃችን አሳልፎ ይሰጣል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም ጉባኤ ሁሉ እግዚአብሔር በሰይፍና በጦር የሚያድን እንዳይደለ ያውቃል። ሰልፉ ለእግዚአብሔር ነውና፤ እግዚአብሔርም እናንተን በእጃችን አሳልፎ ይሰጣል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም ጉባኤ ሁሉ እግዚአብሔር በሰይፍና በጦር የሚያድን እንዳይደል ያውቅ ዘንድ ነው። ሰልፉ ለእግዚአብሔር ነውና፥ እናንተንም በእጃችን አሳልፎ ይሰጣል። |
ከዚህም በኋላ ከተከታዮቹ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሶ መጥቶ፦ “ከእስራኤል አምላክ በቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን እነሆ፥ አሁን ተረዳሁ፤ ስለዚህም ጌታዬ ሆይ፥ እባክህ ይህን ስጦታ ተቀበለኝ” አለው።
በዚህ ጊዜ አሳ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፥ ኀያላኑንም ሠራዊት ሆነ ደካማውንም የመርዳት ችሎታ አለህ፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ በአንተ ስለ ተማመንን እነሆ፥ ይህን ብዙ ሠራዊት ለመውጋት መጥተናልና እባክህ እርዳን፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ አምላካችን ነህ፤ አንተን ማሸነፍ የሚችል ማንም የለም።”
ለንጉሣዊ ሥልጣኑ ወሰን የለውም፤ መንግሥቱም ዘለዓለማዊ ሰላም የሰፈነበት ይሆናል፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም፥ እውነትና ፍትሕ የሰፈነበት መንግሥት በዳዊት ዙፋን ላይ ተመሥርቶ እንዲጸና ያደርገዋል፤ የሠራዊት አምላክ ቅናት ይህን ለማድረግ ወስኖአል።
ለይሁዳ ሕዝቦች ግን ፍቅር አሳያቸዋለሁ፤ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር አድናቸዋለሁ፤ የማድናቸውም በጦርነት ኀይል አይደለም፤ በሰይፍ፥ በቀስትና በፍላጻ ወይም በፈረስና በፈረሰኛ አይደለም።”
ለዘሩባቤል እንዳስታወቀው መልአኩ የነገረኝ የሠራዊት አምላክ ቃል ይህ ነው፤ “ድል የምትነሣው በመንፈሴ እንጂ በኀይልና በብርታት አይደለም።
እግዚአብሔርም ኢያሱን “እነርሱን አትፍራቸው፤ እኔ አንተን በእነርሱ ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ ከእነርሱ አንድም የሚቋቋምህ አይኖርም” አለው።
ዮናታን ጋሻ ጃግሬ የሆነውን ወጣት “ና ወደ እነዚያ ወደ አልተገረዙት ወገኖች የጦር ሰፈር እንሻገር እግዚአብሔር ይረዳን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት እግዚአብሔር ማዳን አይሳነውም” አለው።
ከዚህ በኋላ ሳኦል ዳዊትን እንዲህ አለው፥ “የእግዚአብሔርን ጦርነት በጀግንነት ብትዋጋ ታላቅዋን ልጄን ሜራብን እድርልሃለሁ፤” ሳኦል ይህን ያለበት ምክንያት በፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲሞት እንጂ እርሱ ዳዊትን ለመግደል ስላልፈለገ ነው።