1 ሳሙኤል 17:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልና ወታደሮቹም የፍልስጥኤማዊውን ቃል በሰሙ ጊዜ በፍርሃት ተንቀጠቀጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልና እስራኤላውያን ሁሉ የፍልስጥኤማዊውን ቃል በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ፤ ደነገጡም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልና እስራኤላውያን ሁሉ የፍልስጥኤማዊውን ቃል በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ፤ ደነገጡም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልና እስራኤልም ሁሉ ይህን የፍልስጥኤማዊውን ቃል በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ፤ ደነገጡም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልና እስራኤልም ሁሉ እንዲህ የሚላቸውን የፍልስጥኤማዊውን ቃል በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ፥ ደነገጡም። |
“እኔን ባለማስታወስና ስለ እኔ ባለማሰብ ውሸት የተናገራችሁት ማንን ፈርታችሁ ነው? እኔን ያልፈራችሁኝ ለብዙ ጊዜ ዝም ስለልኩና እንዳላየ ስለሆንኩ ነውን?
ከዕብራውያን መካከል አንዳንዶቹ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ገለዓድ ግዛቶች ሄዱ። ሳኦል ግን እስከዚህ ጊዜ ድረስ በጌልገላ ነበር፤ ከእርሱም ጋር የነበረው ሠራዊት ከፍርሃት የተነሣ ይንቀጠቀጥ ነበር፤
ዳዊት በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም የሚኖር የኤፍራታዊው የእሴይ ልጅ ነበር፤ እሴይ ስምንት ልጆች ያሉት ሲሆን ሳኦል በነገሠበት ዘመን በዕድሜ የገፋ ሽማግሌ ሰው ነበር።
በፊታቸው ጠባዩን ለወጠ፤ ከእነርሱ ጋር እያለም ራሱን እብድ አስመሰለ፤ በበሩ መዝጊያ ላይ ቧጠጠ፤ ለሐጩንም በጺሙ ላይ እንዲዝረከረክ አደረገ።
እስራኤላውያን በምጽጳ መሰብሰባቸውንም ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎች አደጋ ሊጥሉባቸው ወጡ፤ እስራኤላውያንም ይህን በሰሙ ጊዜ ፈሩ።