1 ሳሙኤል 14:47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል በእስራኤል ከነገሠ በኋላ፥ በሁሉም ስፍራ የሚገኙ ጠላቶቹን ወጋ፤ እነርሱም የሞአብ፥ የዐሞንና የኤዶም ሕዝቦች፥ የጾባ ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያን ናቸው፤ በተዋጋበት ስፍራ ሁሉ ድል አድራጊ ሆነ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል በእስራኤል ላይ በትረ መንግሥቱን ከጨበጠ በኋላ፣ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ማለትም ሞዓብን፣ አሞናውያንን፣ ኤዶምን፣ የሱባን ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው። በሄደበት ሁሉ ድል ይነሣ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል በእስራኤል ላይ ከነገሠ በኋላ፥ በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ሞዓብን፥ አሞናውያንን፥ ኤዶምን፥ የጾባን ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው። በተዋጋበት ስፍራ ሁሉ ድል አድራጊ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፤ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከቢዖርም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፥ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ይዋጋ ነበር፥ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር። |
ዐሞናውያን ዳዊትን በገዛ እጃቸው ጠላት እንዳደረጉት ተገነዘቡ፤ ስለዚህም እግረኛ ወታደሮችን ከቤትረሖብና ከጾባ ኻያ ሺህ ሶርያውያንንና ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን፤ እንዲሁም ከንጉሥ ማዕካ አንድ ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ፤
ከዚያም በኋላ ዳዊት የሶርያ ግዛት የሆነችው የጾባ ንጉሥ የሆነውን የረሖብን ልጅ ሀዳድዔዜርን ድል አደረገ፤ ሀዳድዔዜር ድል በተመታበትም ጊዜ በላይኛው ኤፍራጥስ ወንዝ የሚገኘውን ግዛቱን ለማስመለስ በጒዞ ላይ ነበር።
እንደገናም እግዚአብሔር ረዞን ተብሎ የሚጠራውን የኤሊዓዳን ልጅ በሰሎሞን ላይ ጠላት አድርጎ አስነሣ፤ ረዞን የጾባ ንጉሥ ከነበረው ከጌታው ከሀዳድዔዜር ኮብልሎ፥
ይሁን እንጂ እነርሱ ለዘለዓለም ፈጽሞ እንዲደመሰሱ ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ አልነበረም፤ ስለዚህም በዳግማዊ ኢዮርብዓም አማካይነት አዳናቸው።
ከእንግዲህ ወዲህ የሚመራችሁ ንጉሥ አግኝቼአለሁ፤ እኔ ግን ዕድሜዬ ስለ ገፋ ሸምግዬአለሁ፤ ልጆቼም ከእናንተው ጋር አሉ፤ ከወጣትነት ጊዜዬ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የእናንተ መሪ ሆኜ ቈይቼአለሁ።
ሳኦል በነበረበት ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በብርቱ ጠላትነት ሲዋጋ ኖረ፤ ስለዚህም ብርቱ ወይም ጀግና የሆነ ሰው ሲያገኝ እየመለመለ በጦር ሠራዊቱ ውስጥ ያስመዘግበው ነበር።