እግዚአብሔር መላውን ዓለም አተኲሮ በመመልከት፥ በሙሉ ልባቸው በእርሱ ለሚተማመኑት ሁሉ ብርታትን ይሰጣቸዋል፤ እንግዲህ አንተ የሞኝነት ሥራ ስለ ፈጸምክ ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይለይህም፤”
1 ጴጥሮስ 3:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ይመለከታሉ፤ ጆሮዎቹም ጸሎታቸውን ለመስማት ተከፍተዋል፤ በክፉ አድራጊዎች ላይ ግን ጌታ የቊጣ ፊቱን ያሳያል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም የጌታ ዐይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ ጆሮቹም ጸሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፤ የጌታ ፊት ግን በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው፤ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው የተከፈቱ ናቸው፤ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፤ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፤ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፥ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፥ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው። |
እግዚአብሔር መላውን ዓለም አተኲሮ በመመልከት፥ በሙሉ ልባቸው በእርሱ ለሚተማመኑት ሁሉ ብርታትን ይሰጣቸዋል፤ እንግዲህ አንተ የሞኝነት ሥራ ስለ ፈጸምክ ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይለይህም፤”
ይህች ከተማ እንድትጠፋ ወስኛለሁ፤ ፈጽሞም ምሕረት አላደርግላትም፤ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣታለሁ፤ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
እቈጣቸዋለሁ፤ ምንም እንኳ ለጊዜው ከእሳቱ ቢያመልጡ እሳቱ ግን ይበላቸዋል፤ እነርሱንም በምትቈጣበት ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።
ማንም ሰው ከልጆቹ አንዱን ለሞሌክ አሳልፎ በመስጠት የተቀደሰውን ድንኳኔን ቢያረክስና ቅዱስ ስሜንም ቢያሰድብ፥ ያ ሰው በእኔ ፊት የተጠላ ይሆናል፤ ከሕዝቡም ለይቼ አጠፋዋለሁ።
“ማንም ሰው ምክር ለመጠየቅ ወደ ሙታን መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቋዮች ቢሄድ በዚያ ሰው ላይ ቊጣዬን አወርዳለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ፤
ትንሽ ነገር የሚደረግበትን ቀን የናቀ ቱምቢውን በዘሩባቤል እጅ ሲያይ ይደሰታል፤ እነዚህ ሰባቱ መቅረዞች ዓለምን የሚያካልሉ የእግዚአብሔር ዐይኖች ናቸው።”
እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን እንደማይሰማ የታወቀ ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚያመልክና ፈቃዱንም የሚፈጽም ሰው ሲኖር እርሱን እግዚአብሔር ይሰማዋል።
ስለዚህ እንድትፈወሱ ኃጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ እያንዳንዱም ለሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ውጤት የሚያስገኝ ታላቅ ኀይል አለው፤