1 ጴጥሮስ 2:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ምንም ኃጢአት አላደረገም፤ በአፉ ተንኰል አልተገኘበትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እርሱ ኀጢአት አላደረገም፤ በአፉም ተንኰል አልተገኘበትም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ኃጢአት አላደረገም፤ በአፉም ተንኰል አልተገኘበትም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እርሱም ኀጢአት አላደረገም፤ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኵኦልም በአፉ አልተገኘበትም፤ |
ከዚህም በላይ ጲላጦስ በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፦ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ ሌሊት በሕልም ብዙ ተሠቃይቻለሁና በዚያ በንጹሕ ሰው ላይ ምንም እንዳታደርግ” ስትል ላከችበት።
እንዲሁም ክርስቶስ የብዙዎችን ኃጢአት ለማስወገድ አንድ ጊዜ ተሠውቶአል፤ ደግሞም ኃጢአትን ለመሸከም ሳይሆን እርሱን የሚጠባበቁትን ለማዳን ሁለተኛ ጊዜ ይገለጣል።
ልጆቼ ሆይ! ይህን የምጽፍላችሁ ኃጢአት እንዳትሠሩ ብዬ ነው። ነገር ግን ማንም ሰው ኃጢአት ቢሠራ በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፤ እርሱም ጻድቁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።