1 ነገሥት 6:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሕጎቼን፥ ትእዛዞቼንና ሥርዓቴን ሁሉ ብትጠብቅ፥ ለአባትህ ለዳዊት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል ለአንተ አጸናለሁ፤ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ሆኜ አንተ በምትሠራው በዚህ ቤተ መቅደስ ውስጥ እኖራለሁ። ከቶም አልለያቸውም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለምትሠራው ስለዚህ ቤተ መቅደስ ሥርዐቴን ብትከተል፣ ፍርዴን በተግባር ብትገልጸው፣ ትእዛዞቼን ብትጠብቅና ብትመላለስባቸው ለአባትህ ለዳዊት የሰጠሁትን ተስፋ በአንተ እፈጽመዋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስለዚህ ስለምትሠራው ቤት ሕጎቼን፥ ትእዛዞቼንና ሥርዓቴን ሁሉ ብትጠብቅ፥ ለአባትህ ለዳዊት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል ለአንተ አጸናለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ስለዚህ ስለምትሠራልኝ ቤት በሥርዐቴ ብትሄድ፥ ፍርዴንም ብታደርግ፥ ትመላለስባቸውም ዘንድ ትእዛዞቼን ሁሉ ብትጠብቅ፥ ለአባትህ ለዳዊት የነገርሁትን ቃል ከአንተ ጋር አጸናለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “ስለዚህ ስለምትሠራው ቤት በሥርዐቴ ብትሄድ፥ ፍርዴንም ብታደርግ፥ ትመላለስበትም ዘንድ ትእዛዜን ሁሉ ብትጠብቅ፥ ለአባትህ ለዳዊት የነገርሁትን ቃል ከአንተ ጋር አጸናለሁ። |
አሁንም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ለአባቴ ለዳዊት ‘አንተ ታደርግ በነበረው ዐይነት ልጆችህ ታዛዦች ቢሆኑና በፊቴም በቅንነት ቢመላለሱ ሁልጊዜ ከዘርህ በእስራኤል ዙፋን ላይ በፊቴ የሚነግሥ ልጅ አላሳጣህም’ ስትል የተናገርከውን የተስፋ ቃል ፈጽም!
ለእኔ ቤተ መቅደስ የሚሠራልኝ እርሱ ነው፤ እርሱ ልጅ ይሆነኛል፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ መንግሥቱም በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።’ ”
ዳዊት ሰሎሞንንም እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ የአባትህን አምላክ እንድታውቅ፥ በሙሉ ልብና በፈቃደኛ አእምሮ እንድታገለግለው ዐደራ እልሃለሁ፤ እርሱ ሐሳባችንንና ምኞታችንን ሁሉ ያውቃል፤ ወደ እርሱ ብትቀርብ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል፤ ብትተወው ግን እርሱም ለዘለዓለም ይተውሃል፤
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል አለው፦ “አካሄድህ እንደኔ ፈቃድ ቢሆን፥ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብታደርግ፥ በቤተ መቅደሴ የአስተዳዳሪነትን፥ በአደባባዮቼም የበላይነትን ሥልጣን እሰጥሃለሁ፤ እዚህ ከቆሙት መላእክት ጋር በእኔ ፊት መግባትና መውጣት እንድትችል ባለሟልነትን እሰጥሃለሁ።
ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት ጸንታችሁ ስትኖሩ ብቻ ነው፤ ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና በዓለም ላይ ላሉት ሰዎች ሁሉ የተሰበከ ነው፤ እኔ ጳውሎስም አገልጋይ የሆንኩት ለዚሁ ወንጌል ነው።