ከዚህ በኋላ ንጉሥ ኢዮራም “ሠረገላዬን አዘጋጅልኝ” ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ ሠረገላውም ተዘጋጅቶለት እርሱና ንጉሥ አካዝያስ በየግል ሠረገላቸው እየጋለቡ ኢዩን ሊገናኙት ወጡ፤ እነርሱም ኢዩን ቀድሞ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ አገኙት።
1 ነገሥት 21:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናቡቴ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም በኢይዝራኤል በሚገኘው በንጉሥ አክዓብ ቤተ መንግሥት አጠገብ የራሱ ርስት የሆነ አንድ የወይን ተክል ቦታ ነበረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጥቂት ጊዜ በኋላ በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ የወይን ተክል ቦታ ላይ አንድ ነገር ደረሰ፤ ቦታውም በኢይዝራኤል ውስጥ ከሰማርያ ንጉሥ ከአክዓብ ቤተ መንግሥት አጠገብ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሶርያም ንጉሥ የአዴር ልጅ ጭፍራውን ሁሉ ሰበሰበ፥ ከእርሱም ጋር ሠላሳ ሁለት ንጉሦች ነበሩ፥ ፈረሶችና ሰረገሎችም ነበሩ፥ ወጥቶም ሰማርያን ከበበ፥ ወጋትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሶርያም ንጉሥ ወልደ አዴር ሠራዊቱን ሁሉ ሰበሰበ፤ ወጥቶም ሰማርያን ከበባት፤ እየጠበቃቸውም ተቀመጠ። ከእርሱም ጋር ሠላሳ ሁለት ነገሥታት ነበሩ፤ ፈረሶችና ሰረገሎችም ነበሩ፤ ወጥተውም ሰማርያን ከበቧት፥ ወጓትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሶርያም ንጉሥ ወልደ አዴር ጭፍራውን ሁሉ ሰበሰበ፤ ከእርሱም ጋር ሠላሳ ሁለት ነገሥት ነበሩ፥ ፈረሶችና ሰረገሎችም ነበሩ፤ ወጥቶም ሰማርያን ከበበ፥ ወጋትም። |
ከዚህ በኋላ ንጉሥ ኢዮራም “ሠረገላዬን አዘጋጅልኝ” ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ ሠረገላውም ተዘጋጅቶለት እርሱና ንጉሥ አካዝያስ በየግል ሠረገላቸው እየጋለቡ ኢዩን ሊገናኙት ወጡ፤ እነርሱም ኢዩን ቀድሞ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ አገኙት።
ኢዩ ቢድቃር ተብሎ የሚጠራውን የቅርብ ረዳቱን “ሬሳውን አንሥተህ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ ወርውረህ ጣለው፤ እኔና አንተ የንጉሥ ኢዮራም አባት ከነበረው ከአክዓብ በስተኋላ እየጋለብን ስንሄድ እግዚአብሔር በአክዓብ ላይ የተናገረውን ቃል አስታውስ፤
እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።
እስራኤላውያን በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ በሚገኘው ምንጭ አጠገብ ሰፍረው ሳሉ፥ ፍልስጥኤማውያን ወታደሮቻቸውን በአንድነት ሰብስበው በማምጣት በአፌቅ አሰለፉ፤