እንዲሁም ኢዮርብዓም በኮረብታዎች ላይ የማምለኪያ ስፍራዎችን አዘጋጅቶ የሌዊ ነገድ ካልሆኑ ቤተሰቦች መካከል ማንኛውንም ሰው ካህን አድርጎ ሾመ።
1 ነገሥት 14:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለባዕዳን አማልክትም የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤ በኮረብታዎች ላይና በዛፎች ጥላ ሥር የሚያመልኩአቸውን የድንጋይ ቅርጾችንና የአሼራን ምስሎች አቆሙ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም በእያንዳንዱ ኰረብታና በየትልልቁ ዛፍ ጥላ ሥር የማምለኪያ ኰረብቶችን አዕማደ ጣዖታት፣ የአሼራን ምስል ዐምድ ለራሳቸው አቆሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለባዕዳን አማልክትም የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤ በኮረብታዎች ላይና በዛፎች ጥላ ሥር የሚያመልኩአቸውን የድንጋይ ቅርጾችንና የአሼራን ምስሎች አቆሙ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ደግሞ ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ፥ ቅጠሉም ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች መስገጃዎችን ሠሩ፤ ሐውልቶችንና የማምለኪያ አፀዶችንም ለራሳቸው አቆሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ደግሞ ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ፥ ቅጠሉ ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች መስገጃዎችንና ሐውልቶችን የማምለኪያ ዐፀዶችንም ለራሳቸው ሠሩ። |
እንዲሁም ኢዮርብዓም በኮረብታዎች ላይ የማምለኪያ ስፍራዎችን አዘጋጅቶ የሌዊ ነገድ ካልሆኑ ቤተሰቦች መካከል ማንኛውንም ሰው ካህን አድርጎ ሾመ።
እግዚአብሔር እስራኤልን ይቀጣል፤ እርስዋም በውሃ ምንጭ ውስጥ እንደሚንቀጠቀጥ ሸምበቆ ትንቀጠቀጣለች፤ አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ጣዖት በመሥራት ስላስቈጡት፤ የእስራኤልንም ሕዝብ ከዚህች ለቀድሞ አባቶቻቸው ከሰጣቸው ለም ምድር ነቃቅሎ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ እንዲበታተኑ ያደርጋል፤
ንጉሥ አሳ በአሕዛብ የማምለኪያ ቦታዎች የቤተ ጣዖትን አመንዝራዎችን ሁሉ ከሀገሪቱ አስወገደ፤ ከእርሱም በፊት የነበሩ ነገሥታት የሠሩአቸውን ጣዖቶችንም ሁሉ ነቃቅሎ ጣለ።
ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖች ንጉሥ ቤንሀዳድን እንዲህ አሉት፤ “የእስራኤል አማልክት የተራራ አማልክት ናቸው፤ እስራኤላውያን እኛን ማሸነፍ የቻሉት ስለዚህ ነው፤ በሜዳማ ስፍራዎች ጦርነት ብንገጥማቸው ግን እናሸንፋለን፤
ሰሎሞን እግዚአብሔርን ይወድ ነበር፤ የአባቱንም የዳዊትን መመሪያ ይጠብቅ ነበር፤ ይሁን እንጂ እንስሶችን እያረደ በተለያዩ ኰረብቶች ላይ መሥዋዕት ያቀርብ፥ ዕጣንም ያጥን ነበር።
የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ በመጣስ የሚሰግዱላቸውን ከወርቅ የተሠሩ ሁለት ጥጆችን አቆሙ፤ እንዲሁም አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ሠሩ፤ ለከዋክብት ሰገዱ፤ ባዓል ተብሎ ለሚጠራውም ባዕድ አምላክ አገልጋዮች ሆኑ።
ነገር ግን የይሁዳ ሰዎችም ቢሆኑ፥ አምላካቸው እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዞች አልጠበቁም ነበር፤ እነርሱም የእስራኤል ሕዝብ የተቀበሉትን ልማድ ተከታዮች ነበሩ።
ስለዚህ ሰዎቹም በቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ መስገድ ትተው፥ አሼራ ተብላ ለምትጠራ ሴት አምላክ ጣዖቶችና ምስሎች መስገድ ጀመሩ። ይህንንም ኃጢአት በመሥራታቸው የእግዚአብሔር ቊጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ወረደ።
እናንተ በዋርካ ዛፎች መካከልና በየለምለሙ ዛፍ ሥር በፍትወት የምትቃጠሉ ናችሁ፤ እንዲሁም በሸለቆዎች ውስጥ በቋጥኞች መካከል ልጆቻችሁን ለዕርድ ታቀርባላችሁ።
በመላ አገራችሁ፥ በኮረብቶችና በተራሮች ላይ እንዲሁም በታላላቅ ዛፎች ሥር ሕዝቡ በየትውልዱ መሠዊያዎችንና የተለዩ ዐምዶችን አቁሞ አሼራ ተብላ ለምትጠራው ጣዖት ይሰግዳሉ።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ሆይ! ከብዙ ጊዜ በፊት ለኔ መታዘዝና እኔን ማገልገል ትተሻል፤ በእርግጥም በተራራው ላይና በየዛፉ ጥላ ሥር ሌሎች አማልክትን በማምለክ አመንዝረሻል።
አንቺ በደለኛ መሆንሽንና በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ ማመፅሽን ብቻ እመኚ፤ ከባዕዳን አማልክት ጋር በየለምለሙ ዛፍ ሥር የጣዖት አምልኮ ርኲሰት መፈጸምሽንና ለሕጌም ያለመታዘዝሽን ተናዘዢ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
ሬሳዎች በጣዖቶችና በመሠዊያዎች ዙሪያ ይከመራሉ፤ በከፍተኛ ኰረብቶችና በተራሮች ጫፍ ላይ፥ እንዲሁም በየለምለሙ ዛፍና በየትልልቁ ወርካ ሥር ለጣዖቶቻቸው መልካም ሽታ ባቀረቡባቸው ስፍራዎች ሁሉ ሬሳዎች ይወድቃሉ፤ በዚያን ጊዜ ሰዎች ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።
የእስራኤል ተራራዎች የልዑል እግዚአብሔርን ቃል እንዲሰሙ ንገራቸው፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምናገረውን ተራራዎች፥ ኮረብቶችንና ገደላማ ሸለቆዎች ሁሉ ይስሙ፤ ሕዝቦች ለጣዖቶች የሚሰግዱባቸውን ከፍተኛ ቦታዎች ሁሉ የሚያጠፋ ሰይፍ እልካለሁ።
የምትኖሩባቸው ከተሞቻችሁ ሁሉ ባድማ ይሆናሉ፤ የመስገጃ ከፍተኛ ቦታዎቻችሁም ይፈርሳሉ፤ መሠዊያዎቻችሁ ፈርሰው ውድማ ይሆናሉ፤ ጣዖቶቻችሁ ተንኰታኲተው ይወድቃሉ፤ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁም ይሰባበራሉ፤ የሠራችሁት ነገር ሁሉ እንዳልነበረ ይሆናል።
የእስራኤል ሕዝብ ብዙ ዘለላ እንደ ያዘ የወይን ተክል ናቸው፤ ፍሬ በበዛላቸው መጠን ብዙ የጣዖት መሠዊያዎችን ሠሩ፤ ምድራቸው ፍሬያማ ሆና በበለጸገችላቸው መጠን የጣዖት መስገጃ ዐምዶችን አስጊጠው ሠሩ።
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ትሰግዱላቸው ዘንድ ማናቸውንም ዐይነት ጣዖቶች አትሥሩ፤ እንዲሁም ምስል ወይም ሐውልት ወይም የተቀረጸ የድንጋይ ዐምድ አታቁሙ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤