Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 15:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ንጉሥ አሳ በአሕዛብ የማምለኪያ ቦታዎች የቤተ ጣዖትን አመንዝራዎችን ሁሉ ከሀገሪቱ አስወገደ፤ ከእርሱም በፊት የነበሩ ነገሥታት የሠሩአቸውን ጣዖቶችንም ሁሉ ነቃቅሎ ጣለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የቤተ ጣዖት ወንደቃዎችን ከምድሪቱ አባረረ፤ አባቶቹ የሠሯቸውን ጣዖታት ሁሉ አስወገደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ንጉሥ አሳ በአሕዛብ የማምለኪያ ቦታዎች የቤተ ጣዖትን አመንዝራዎችን ሁሉ ከሀገሪቱ አስወገደ፤ ከእርሱም በፊት የነበሩ ነገሥታት የሠሩአቸውን ጣዖቶችንም ሁሉ ነቃቅሎ ጣለ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከሀ​ገ​ሩም የጣ​ዖ​ታ​ትን ምስል ሁሉ አስ​ወ​ገደ፥ አባ​ቶ​ቹም የሠ​ሩ​አ​ቸ​ውን ጣዖ​ታ​ትን ሁሉ አጠፋ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከአገሩም ሰዶማውያንን አስወገደ፤ አባቶቹም ያደረጉትን ጣዖታትን ሁሉ አራቀ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 15:12
14 Referencias Cruzadas  

አቢያም፥ እንደ ታላቁ አያቱ እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ታማኝ ሆኖ በመገኘት ፈንታ፥ አባቱ ሮብዓም ይፈጽመው የነበረውን ኃጢአት ሁሉ መሥራቱን ቀጠለ።


አክዓብ ከፈጸመው አሳፋሪ በደል ሁሉ ዋናው ክፍል እስራኤላውያን ወደ ምድረ ርስት በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ከፊታቸው ነቃቅሎ ያባረራቸው አሞራውያን ያደርጉት በነበረው ዐይነት ጣዖት ማምለኩ ነው።


ከአባቱ ከአሳ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ የተረፉትንና በአሕዛብ የማምለኪያ ቦታዎች ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ ወንዶችና ሴቶች አመንዝራዎችን ሁሉ አስወገደ።


በዚያን ዘመን የኤዶም ምድር የራስዋ ንጉሥ አልነበራትም፤ ከዚህም የተነሣ በይሁዳ ንጉሥ በሚሾመው እንደ ራሴ ትገዛ ነበር።


ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ ወንዶች በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚያገለግሉበትንና ሴቶችም አሼራ ተብላ ለምትጠራው ሴት አምላክ መጋረጃ የሚፈትሉበትን ክፍል ሁሉ ደመሰሰ።


“እስራኤላዊ የሆነ ማንኛውም ወንድ ወይም ሴት የቤተ ጣዖት ተከታዮች እንደሚያደርጉት የዝሙት ሥራ አይፈጽሙ፤


እናንተ ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ አኗኗር የተዋጃችሁት ጠፊ በሆነ በብር ወይም በወርቅ አለመሆኑን ታውቃላችሁ።


በዚሁ ዐይነት ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸው ያሉ ከተሞችም ሴሰኞች ሆኑ፤ ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪም ዝሙት ፈጸሙ። ስለዚህ እነርሱ በዘለዓለም እሳት ለሚቀጡት ምሳሌ ሆነዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos