1 ነገሥት 13:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከይሁዳ ለመጣው የእግዚአብሔር ሰው እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዝ ባለመታዘዝ የእግዚአብሔርን ቃል አላከበርክም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከይሁዳ ለመጣውም የእግዚአብሔር ሰው፣ “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፣ ‘የእግዚአብሔርን ቃል አቃልለሃል፤ አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህንም ትእዛዞች አልጠበቅህም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከይሁዳ ለመጣው ለእግዚአብሔር ሰው እንዲህ አለው፤ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ጌታ አምላክህ ያዘዘህን ትእዛዝ ባለመታዘዝ የጌታን ቃል አላከበርክም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከይሁዳም የመጣውን የእግዚአብሔርን ሰው እንዲህ አለው፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእግዚአብሔር ቃል ላይ አምፀሃልና፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ያዘዘህን ትእዛዝ አልጠበቅህምና፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከይሁዳም ወደ መጣው ወደ እግዚአብሔር ሰው “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘በእግዚአብሔር አፍ ላይ ዐምፀሃልና፥ አምላክህም እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዝ አልጠበቅህምና፥ |
ጋድ ወዶ እርሱ ቀርቦ እግዚአብሔር ስለ እርሱ ያለውን ነገረው፤ ቀጠል አድርጎም “በምድርህ ሦስት ዓመት ራብ ከሚሆን፥ ለሦስት ወር ጠላቶችህ ከሚያሳድዱህና በምድርህ ላይ ለሦስት ቀን የቸነፈር መቅሠፍት ከሚሆን የትኛውን ትመርጣለህ? እንግዲህ በብርቱ አስብበትና ወደ እግዚአብሔር የማቀርበውን መልስ ስጠኝ” ሲል ጠየቀው።
ይህን በማድረግ ፈንታ እኔ በዚያ ምንም ዐይነት እህል ውሃ እንዳትቀምስ ወዳዘዝኩህ ቦታ ተመልሰህ በላህ፤ ይህንንም በማድረግህ ምክንያት ትገደላለህ፤ ሬሳህም በቤተሰብህ መቃብር አይቀበርም።’ ”
ስለዚህም ያ ነቢይ “የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መፈጸም እምቢ ስላልክ፥ ከእኔ ተለይተህ እንደ ሄድክ ወዲያውኑ አንድ አንበሳ ይገድልሃል” አለው፤ በእርግጥም ከእርሱ ተለይቶ እንደ ሄደ አንበሳ በድንገት ወደ እርሱ መጥቶ ገደለው።
ለሚስቱና ለወዳጆቹም የደረሰበትን አሳፋሪ ነገር በሙሉ ነገራቸው፤ ሚስቱና እነዚያ አስተዋዮች የሆኑ ወዳጆቹም “እነሆ በገዛ እጅህ ሥልጣንህን ለመርዶክዮስ ልታስረክብ ተቃርበሃል፤ እርሱ አይሁዳዊ ስለ ሆነ ልትቋቋመው አትችልም፤ በእርግጥም እርሱ ያሸንፍሃል!” አሉት።
እነሆ የራስሽ ክፋት ይቀጣሻል፤ ክሕደትሽ ይፈርድብሻል፤ እኔን አምላክሽን እግዚአብሔርን መተውሽና ለእኔም የምታሳዪውን ክብር ማስቀረትሽ ምን ያኽል ከባድና መራራ በደል እንደ ሆነ ትረጂአለሽ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ጌታ የሠራዊት አምላክ ነኝ።”
ሙሴም አሮንን “እግዚአብሔር ‘በፊቴ ቀርቦ የሚያገለግለኝ ሁሉ ቅድስናዬን ያክብር፤ እኔም በሕዝቤ ፊት የተከበርኩ እሆናለሁ’ እያለ በተናገረበት ጊዜ ይህንኑ ማስጠንቀቁ ነበር” አለው። አሮንም መልስ ሳይሰጥ ዝም አለ።
ነገር ግን እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ገሠጻቸው፤ “በእስራኤላውያን ፊት የተቀደሰ ክብሬን ትገልጡ ዘንድ ስላላመናችሁብኝ፥ ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር የዚህ ሕዝብ መሪዎች ሆናችሁ አትገቡም።”
“አሮን ለእስራኤላውያን ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር አይገባም፤ እናንተ ሁለታችሁ በመሪባ ውሃ ዘንድ በትእዛዜ ላይ ስላመፃችሁ አሮን ይሞታል።
ወሬ ነጋሪው የቃል ኪዳኑን ታቦት መማረክ ባወሳ ጊዜ ዔሊ በቅጽሩ በር አጠገብ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ተገልብጦ ወደ ኋላው ወደቀ፤ እርሱም ሽማግሌ ከመሆኑም በላይ በውፍረቱ ግዙፍ ስለ ነበር ከአወዳደቁ የተነሣ አንገቱ ተሰብሮ ሞተ፤ ዔሊም በእስራኤል መሪ ሆኖ የቈየበት ዘመን አርባ ዓመት ነበር።