1 ዮሐንስ 4:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወዳጆች ሆይ! ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ እርስ በርሳችን እንፋቀር፤ የሚያፈቅር ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ እግዚአብሔርንም ያውቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወዳጆች ሆይ፤ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ እርስ በርሳችን እንዋደድ፤ የሚወድድ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ ነው፤ እግዚአብሔርንም ያውቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ፤ የሚያፈቅር ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ ነው፥ እግዚአብሔርንም ያውቃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ። |
“ብርሃን በጨለማ ውስጥ ይብራ!” ብሎ የተናገረ እግዚአብሔር በክርስቶስ መልክ የሚያበራውን የእግዚአብሔርን ክብር የማወቅ ብርሃን እንዲሰጠን ብርሃኑን በልባችን ውስጥ እንዲበራ አደረገ።
አሁን ግን እግዚአብሔርን ዐውቃችኋል፤ ይልቁንም እግዚአብሔር እናንተን ዐውቋችኋል፤ ታዲያ፥ ወደ እነዚያ ወደ ደካሞችና ወደማይረቡት የዓለም ሥርዓቶች እንዴት ተመለሳችሁ? እንዴትስ እንደገና የእነርሱ ባሪያዎች ለመሆን ትፈልጋላችሁ?
አምላክህ እግዚአብሔር ለአንተና ለልጆችህ ታዛዥ ልብ ይሰጣል፤ ስለዚህም እርሱን በፍጹም ልብህ ትወደዋለህ፤ በዚያችም ምድር በሕይወት ትኖራለህ።
ለምእመናን ቅንነት የተሞላበት ፍቅር እንዲኖራችሁ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችኋል፤ ስለዚህ በሙሉ ልባችሁ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።
ወዳጆቼ ሆይ! ይህ የምጽፍላችሁ ትእዛዝ ከመጀመሪያው አንሥቶ የነበራችሁና የዱሮ ትእዛዝ ነው እንጂ አዲስ አይደለም፤ ይህም የዱሮ ትእዛዝ የሰማችሁት ቃል ነው።
ስለዚህ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር እናውቃለን፤ እናምናለንም። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።
እመቤት ሆይ፥ አሁንም ዐደራሽን፥ ይህ የምጽፍልሽ አዲስ ትእዛዝ አይምሰልሽ፤ አሁን የምጽፍልሽ “እርስ በርሳችን እንዋደድ” የሚለውን ከመጀመሪያ አንሥቶ በእኛ ዘንድ የነበረውን ትእዛዝ ነው።