1 ቆሮንቶስ 10:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ምድርና በእርስዋም ያለው ሁሉ የጌታ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ምድርና በርሷ ያለው ሁሉ የጌታ ነውና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድር የጌታ ነውና፥ በእርሷ የሞላባት ሁሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ምድር በመላዋ የእግዚአብሔር ናትና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድርና በእርስዋ የሞላባት ሁሉ የጌታ ነውና። |
ሙሴም ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “ከከተማው እንደ ወጣሁ እጄን ዘርግቼ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ነጐድጓዱም ይቆማል፤ በረዶም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም፤ በዚህ ዐይነት አንተም ምድር የእግዚአብሔር እንደ ሆነች ታውቃለህ።
የዚህ ዓለም ሀብታሞች እንዳይታበዩ ወይም ተስፋቸውን አስተማማኝ ባልሆነ ሀብት ላይ እንዳያደርጉ እዘዛቸው፤ እንዲሁም ተስፋቸው እኛን ደስ እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር ላይ እንዲሆን እዘዛቸው።